Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 011-67363 28
  • Website
  • Deadline17 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO
  • opening date08/04/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Sector Water Well Drilling

በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሻሎ ዌል (Shallow Well) ቁፋሮና ሙሉ ኢንስታሌሽን ስራን በወረዳው ቀበሌዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያወጣው ማስታወቂያ።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ የተጫራቾች መመሪያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ሻሎዌል (Shallow well) ቁፋሮ እና ሙሉ ኢንስታሌሽን በጅዳ ወረዳ ቀበሌዎች ውስጥ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል በዚሁ መሰረት ፤- የጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት ሻሎዌል (Shallow well) ቁፋሮ እና ሙሉ ኢንስታሌሽን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስቆፈር እና ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም አስፈላጊውን የሰው ሀይል እና ማቴሪያል አሟልቶ ለማሰራት ፍቃደኛ የሆኑትን የሥራ ተቋራጮችን ይጋብዛል። በዚሁ መሠረት የጨረታ ተሳታፊ መሆን የሚፈልጉ መወዳደር እንዲችሉ ፤-

  1. ድርጅቱ ለ2019 የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣የግብር ክሊራንስ (tax clearance) እና (Tin number) ቲን እና (Drilling license) እና በቡሩ ዘርፍ(Drilling well) 5 ደረጃ እና ከዚያ በላይ ያለው መሆን አለበት እንዲሁም ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ፍቃድ በውሃ ጉድጓድ (water well) ዘርፍ ያለው መሆን አለበት ።
  2. ማንኛውም ተጫራች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ (ማለትም ከ2014-2018 ዓ.ም ድረስ)የሚያሳይ የስራ ልምድ (water well Drilling license) ከሚመለከተው አካል ላይ ማቅረብ አለበት እንዲሁም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  3. ማንኛውም ተጫራች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው 5 እና ከዛ በላይ (1-5)የሚያሳይ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ በውሃ ጉድጓድ ዘርፍ (water well Drilling license) ማቅረብ አለበት።
  4. ማንኛውም ተጫራች ለውሃ ጉድጓድ water well ቁፋሮ የሚያገለግል ማሽን ያለው መሆኑን የሚያሳይ ሊብሬ(libre) ያለው ወይም ውክልና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት
  5. ተጫራቹ ለውሃ water well 60 ሜትር ወደ ታች መቆፈር ያለበት ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ 10 ሜትር ጥልቀቱን መጨመር ወይም መቀነስ (60+-10) ይችላል።
  6. ተጫራቹ ለውሃ water well ቁፋሮ የሚያገለግሉ ሁሉንም የማሽን አይነት ያለውና የድርጅቱን የሰው ሀይል እና የስራ ድርሻውን የሚገልፅ ፕሮፋይል ማቅረብ የሚችል።
  7. ተጫራቹ ለውሃ water well ቁፋሮ apron (well head) የሚያገለግሉ ሁሉንም ዕቃዎችን እና ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ለራሱ ማቅረብ አለበት።
  8. ተጫራቹ የእጅ ዋጋ እና የእቃ ዋጋ (material cost and labour cost) አንድ ላይ መሙላት አለባቸው።
  9. ተጫራቹ Well completion report and water test quality report ) ማቅረብ አለበት።
  10. ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር )ብቻ በህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) በጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት በማለት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባታል።
  11. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶችን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በሰም ለየብቻ በማሸግ እና CPO ለብቻ በማሸግ እነዚህን 3 ዶክመንቶች በአንድ ፖስታ (mother envelope) በሰም በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  12. አሸናፊው ድርጅት ለስራ ማስጀመሪያ ቅድመ ክፍያ(Advance payment) ለመውሰድ ከማንኛውም ባንክ( unconditional bank guarant )ማቅረብ አለበት።
  13. አሸናፊው ድርጅት ለስራው ክፍያ ሰነድ( payment certificate)በአግባቡ ሞልቶ ማቅረብ አለበት።
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ተጫራቾች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 07/04/2019 ዓ.ም. ድረስ በጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  16. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ እስከ 08/04/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  17. ጨረታው በዚሁ እለት ማለትም በ08/04/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
  18. ተጫራቾች የተሟላ ሰነድ መያዛቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።
  19. ከጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  20. ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ CPO/ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
ስ.ቁ 011-67363 28

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት

Summary
Jida Woreda Water and Energy Office (North Shewa, Oromia) seeks contractors to drill shallow water wells (about 60 m) with full installation in woreda kebeles. Drilling contractors grade 5 and above with 5 years of experience, own rig, VAT, TIN and tax clearance may bid.
Save Tender