Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Land Bureau (የኦሮሚያ መሬት ቢሮ)
  • Address ሳርቤት አደባባዩን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፓልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910622700
  • Websitehttps://oromialand.et/
  • Deadline02 Dec 2026, 1:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Security250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ CPO
  • opening dateህዳር 23/2019 ዓ.ም በ8:00 ሰዓት ይከፈታል።
  • Sector Stationery Materials , Printer And Photocopy Machine

የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ለመሥሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፕሎተር ቀለም (Plotter Ink) እና የፕሪንተር ቶነር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር NCB/07/2019)።

Oromia Land Bureau (የኦሮሚያ መሬት ቢሮ)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ቁጥር NCB/07/2019 ለመሥሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የፅፈት መሣሪያ፣ የፕሎተሪ ቀለም (plotter ink) እና የፕሪንተር ቶነሪ ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  • ድርጅቶች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ውል ገብተው በተባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ሙሉ በሙሉ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / TIN NO/ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  • ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር/ 100/መቶ/ በመክፈል በኦሮሚያ መሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ለመወዳደር ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የእቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን፣ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንቶችን የራሳቸውን የፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒውን ዶክመንቱን በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 23/2019 ዓ.ም ከቀኑ በ7:30 ሰዓት ተዘግቶ በ8:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  • የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • የጨረታው አሸናፊ አካል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ጨርሶ ማስረከብ የሚችል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ /0949445729/ 0910622700/0919519951/0946653304

አድራሻ:- ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፋልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ

የኦሮሚያ መሬት ቢሮ

Summary
Oromia Land Bureau buys assorted stationery, plotter ink and printer toner by open tender (NCB/07/2019). Suppliers with paid taxes, VAT and TIN who are on the supplier list may bid.
Save Tender