ወማ ሁለገብ የህብረት ስራ ማህበር የአፈር ማዳበሪያ (ዳፕና ዩሪያ) ማጓጓዝ አገልግሎት
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ወማ ሁለገብ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር ኃላ/የተወሰነ
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 001/2019
ወማ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን /ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በቀቤና ልዩ ወረዳ በሚገኘው ቀበሌዎች ውስጥ ያሉ አርሶ አደሮች በያዝነው በ2019/20 ምርት ዘመን በወልቂጤ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘን ወደ ማራገፊያ ጣቢያዎች በበልግና በመኸር ዳፕ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
ስለሆነ ተጫራቾች ከወማ የገ/ህ/ስ/ዩኒየን (ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበር) በእያንዳንዱ ቀበሌ የሚገኙ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈለገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፓልት መንገድ በአማካኝ በኩ/ል በ1 (አንድ) ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዝርዝር መስፈርት
ክፍል አንድ አጠቃላይ የህግ እና የአሰራር መስፈርቶች
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፤ የዘመኑ ግብር ከፍሎ ያሳደሰ እና እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው።
- ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- የስራ ልምድ፡- ተጫራቹ በተለይ የግብርና ግብአቶችን (ማዳበሪያን) (ተመሳሳይ የጅምላ ጭነቶችን በማጓጓዝ ረገድ ቢያንስ የሁለት አመት ልምድ ያለው መሆን አለበት ከቀድሞ ደንበኞችን መልካም የስራ አፈጻጸም ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቹ ስራውን ለሌላ አካል በንዑስ ውል (subcontracting) ማስተላለፍ አይፈቀድለትም። በራሱ የሰራተኛን የተሽርካሪ አቅም ማሟላት አለበት።
- የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲመች በአንድ ልዩ ወረዳ በከፍል ዋጋ ማቅረብ እና መወዳደር አይችልም።
- አጎራባች ወረዳዎችን ያሸነፈ የትራንስፖርት ድርጅቶች የተለያዩ በመሆናቸው ምክንያት በአጎራባች ወረዳዎች ስር በሚገኙ ማራገፊያ ጣቢያዎች መካከል የትራንስፖርት ዋጋ ልዩነት ከተፈጠረ ኪሎ ሜትርን መሰረት በማድረግ በአንድ ኪሎ ሜትር በተሰጠ ዝቅተኛ አማካኝ የአሸናፊ ዋጋ ይስተካከላል።
- ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 10 ሥራ ቀናት መሁኑንና ጨረታው የሚከፈተው በቀን 17/3/2019 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን።
ወማ ሁለገብ ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር
Summary
Wema multipurpose cooperative union (Kebena special woreda) seeks transporters to carry DAP and urea fertilizer from its central warehouse in Wolkite to unloading stations in kebeles. Open bid.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
