Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያና የፕሪንተር ቀለም፣ የፅዳት ዕቃዎች እና ቆሎ የታሸገ ውሃ ኩኪስና ቡና በ3 ሎቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር ኢፕድ 0013/2019)።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር -ኢፕድ 0013/2019

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የፅዳትና የፅህፈት መሳሪያና የፕሪንተር ቀለም ቆሎ የታሸገ ውሃ ኩኪስ እና ቡና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1፦ የፅህፈት መሳሪያ እና የፕሪንተር ቀለም
  • ሎት 2፦ የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3፦ ቆሎ የታሸገ ውሃ ኩኪስ እና ቡና

በዚህም መሰረት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በዉድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

  1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ግዥዉን አስመልክቶ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመዉሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸዉን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀዉ በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።
  3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚዉል ብር፦ ለሎት 1፡- 20,000 (ሃያ ሺህ)፣ ለሎት 2፡- 15,000 (አስራ አምስት ሺህ)፣ ለሎት 3፡- 30,000 (ሰላሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድቦንድ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸዉ አካል የሚሰጥ ዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ አለባቸው።
  4. ጨረታዉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4:30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለዉ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር: 011 1 56 98 69
ኢ.ሜይል: procurement@press.et
አድራሻ: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊትለፊት

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Summary
Ethiopian Press Corporation re-tenders, in 3 lots, stationery and printer toner, cleaning items, and roasted grain (kolo), bottled water, cookies and coffee. Licensed suppliers with TIN, VAT, tax clearance and government supplier registration may bid.
Save Tender