Tender Detail

Tender Details

  • Company ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዲቨሎፕመንት ኢኒሸቲቭ
  • Address መስቀል ፍላወር አካባቢ ያሬድ ቤ/ክ ጀርባ በሚገኘው ዋና መ/ ቤት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 558 40 94
  • Website
  • Deadline22 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price300(ሦስት መቶ ብር)
  • Bid Securityከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 3% በHUNDEE Oromo Grassroots Development Initiative ስም CPO ወይም የባንክ ዋስትና
  • opening dateበዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • Categories Water Pipes And Fittings , Pumps, Motors And Compressors , Agricultural Materials , Machinery And Vehicles

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ (HUNDEE) በADEY ፕሮጀክት በሱሉልታ፣ ዉጫሌ፣ ኤጀርሳ ላፎ፣ ዳንዲ፣ አምቦ፣ ሊበን ጃዊ፣ ኢሉ ገላንና ባኮ ቲቤ ወረዳዎች ለሚገኙ የወጣቶች ቡድኖች የሞተር ፓምፖችን ከውሃ መሳቢያና መልስ ማስወጫ ቱቦዎች ጋር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዲቨሎፕመንት ኢኒሸቲቭ


የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ (HUNDEE Oromo Grassroots Development Initiative) ከMastercard Foundation በATi በኩል በሚደረግ አጋርነት Agriculture-focused Dignified Employment for Youth in Ethiopia (ADEY) የተሰኘውን ፕሮጀክት እየተገበረ ይገኛል። ፕሮጀክቱ ወጣቶችን በተለያዩ የሥራ ዕድሎች ላይ በማሳተፍ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፣ ከዋና ዋና ተግባራቱ አንዱም የወጣቶችን ቡድኖች በማቋቋምና በማጠናከር የተመረጡ የሰብል ምርቶችን በማምረት ላይ እንዲሰማሩ ማስቻል ነው።

በዚህ መሠረት HUNDEE በሱሉልታ፣ ዉጫሌ፣ ኤጀርሳ ላፎ፣ ዳንዲ፣ አምቦ፣ ሊበን ጃዊ፣ ኢሉ ገላንና ባኮ ቲቤ ወረዳዎች ለሚገኙ የተደራጁ የወጣቶች ቡድኖች በበጋ ወቅት የተመረጡ ሰብሎችን በመስኖ ለማልማት የሚያስችሉ የሞተር ፓምፖችን ከውሃ መሳቢያና መልስ ማስወጫ ቱቦዎች ጋር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ፓምፖቹ ወጣቶች ግድቦችን በሠሩባቸው ወንዞች ውስጥ የሚገኘውን ውሃ በመሳብ ለመስኖ እንዲጠቀሙ የሚያስችሉ ናቸው።

የዕቃዎቹ ብዛት፣ ዝርዝር መግለጫ፣ ቴክኒካዊ መስፈርቶችና የማቅረቢያ ሁኔታዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የተገለጹ ይሆናሉ።

በዚህ ዓይነት የዕቃ አቅርቦት ሥራ ላይ ልምድ ያላቸው፣ የታደሰና ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ተገቢውን የግብር ክሊራንስና በጨረታ ሰነዱ የተጠየቁ ሌሎች ሰነዶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎች የጨረታ ሰነዱን በ300.00 (ሦስት መቶ) ብር በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ።

ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 3% (ሦስት በመቶ) የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) HUNDEE Oromo Grassroots Development Initiative ስም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በታሸገው የጨረታ ማቅረቢያ ኤንቨሎፕ ውስጥ ማካተት አለባቸው።

የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማቅረብ የሚቻለው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ፣ መስቀል ፍላወር አደባባይ አካባቢ፣ ከቪላ ቨርዴ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ማቅረብ ይቻላል። ጨረታው በሰባተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፣ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ:- 011 558 3967 / 011 558 2328 / 0913 399 817

✨ messages.ai_summary
HUNDEE Oromo Grassroots Development Initiative buys motor pumps with suction and delivery hoses for youth groups doing dry-season irrigation in eight Oromia woredas (Sululta, Wuchale, Ejersa Lafo, Dendi, Ambo, Liben Jawi, Ilu Gelan, Bako Tibe). Experienced licensed suppliers.
Save Tender