ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ቤቶችን መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል::
Public Service Transport Service (ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 005/2019 ዓ.ም
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ቤቶችን መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል::
ሎት 1 የዋና መስሪያ ቤት ሱቆች ኪራይ አገልግሎት፤
ሎት 2 የቃሊቲ መናኸሪያ ቤቶች፤
ሎት 3 የሸበሌ ማደያ፤
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የስራ ቀናት ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ለእያንዳንዱ ሎት 1000 በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ::
- ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ምዝገባና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያለቸው፤ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በአንድ ፖስታ በማዘጋጀትና በኢንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 20,000(ሃያ ሺ ብር) ሲፒኦ /Bid Bond/ ወይም በባንክ የተመሰከረለት በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በ8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል።
- አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር:- 011-5-50-45-64
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
✨ messages.ai_summary
Public Service Transport Service invites bids to rent out its head office shops, Kality bus station premises and the Shebele fuel station, in 3 lots. Open bid.
