የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሚያካሂዳቸው የምርጫ ተከታታይ ቀሪና ደጋሚ ምርጫ የድጋሚ የኪራይ አገልግሎት ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ ብር 200.00 (ብር ሁለት መቶ) በመከፈል ከቦርዱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፦ NEBE/NCB/ 03/2045
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሚያካሂዳቸው የምርጫ ተከታታይ ቀሪና ደጋሚ ምርጫ የድጋሚ የኪራይ አገልግሎት ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ ብር 200.00 (ብር ሁለት መቶ) በመከፈል ከቦርዱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም ከ ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ክሊራንስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን አንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያነት ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ) በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ከ ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ድረስ ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው መስከረም 18 ቀን 2019 ከሰዓት በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦርዱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- በጨረታው መከፈቻ ላይ የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- ቦርዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አድራሻ ቦሴ መንገድ ፍላሚንጎ ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻችን፡- ቦሴ መንገድ ፍላሚንጎ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- +251 115153468
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
✨ messages.ai_summary
Ethiopia's National Election Board seeks vehicle rental services for its remaining and repeat elections. Bidders must submit separate technical and financial proposals, hold a renewed trade license, VAT and tax registration, tax clearance, and PPAA registration, plus a signed anti-fraud declaration.
