ድርጅታችን ህሊና ገንቢ ምግቦች ኃ/የተ/የግል ማህበር ላለፉት 28 ዓመታት በከፍተኛ ጥራት የነፍስ አድር ምርት ማለትም ፕላምፒነት እያመረተ ለእርዳታ ድርጅቶች ሲያቀርብ ቆይቷል እያቀረበም ይገኛል፡፡ አሁን ደግሞ ለሰፊው ገበያ የሚውል በከፍተኛ ጥራትና ደህንነት የሚመረት ማለዳ የሚባል የለውዝ ቅቤ ይዞ መጥቷል፡፡ ይህን ምርት የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርትን የሚያሟላ እና በከፍተኛ ጥንቃቄ የተመረተ ጣፋጭ ለጤና ተስማሚ የለውዝ ቅቤ ነው፡፡