ዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ትርፋማ ያልሆነ በሲቪል ማህበር ድርጅት ኤጀንሲ እ.ኤ.አ. 2004 ተመዝግቦ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እያደረገ ያለ የውጭ ድርጅት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ድርጅቱ ለሚሰራዉ የህብረተሰብ አቀፍ ፕሮጀክቶች ግብዓት የሚሆን የተለያዩ የአትክልት ዘሮችን የሚያቀርቡ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ስለፈለገ በዝርዝሩ መሰረት ማቅረብ የምትችሉ አቅራቢዎችን ማወዳደር ይፈልጋል፡፡ የአትክልት ዘሮቹ ዓይነትና ዝርዝር ከዚህ በታች በሠንጠረዡ ዉስጥ ተዘርዝረዋል፡፡