Tender Detail

Tender Details

  • Company Hope Enterprises
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline20 Nov 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400(አራት መቶ ብር)
  • Bid Securityእያንዳንዱ ተጫራች የሚያቀርበውን ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ብቻ በድርጅቱ ስም
  • opening dateሕዳር 14/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይከፈታል።
  • Categories Accounting & Auditing , Audit Service

ተስፋ ድርጅት (HOPE Enterprises) የ2024 እና 2025 የበጀት ዓመት የፕሮጀክቶቹን የሂሳብ መግለጫዎች ለማስመርመር ብቁ ኦዲተሮችን በምርመራ (Investigative) ኦዲት አገልግሎት ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያወጣው ማስታወቂያ።

Hope Enterprises


የምርመራ (Investigative) ኦዲት አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

ተስፋ ድርጅት በሲቪል ማህበራት ኤጀንሲ በመዝገብ ቁጥር 0452 የተመዘገበ ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን፣ በሀገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና በሲዳማ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉት ቅርንጫፎች በትምህርት፣ በሙያ ሥልጠና እና በተለያዩ የልማት ሥራዎች የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ድርጅቱ እ.ኤ.አ የ2024 እና 2025 የበጀት ዓመት ያለውን የፕሮጀክቶቹን የሂሳብ መግለጫዎች ለመመርመር ብቁ ኦዲተሮችን አጫርቶ ለማሰራት ይፈልጋል።

I. የሥራ ወሰን፤

  • እ.ኤ.አ የ2024 የበጀት ዓመት ከጃንዋሪ 1 እስከ ዲሴምበር 31/2024 እና
  • እ.ኤ.አ የ2025 የበጀት ዓመት ከጃንዋሪ 1 እስከ ዲሴምበር 31/2025

II. ብቁነት እና ቴክኒካዊ መስፈርቶች፤

ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች የሚከተሉትን ሰነዶች ከቴክኒካል ፕሮፖዛላቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:-

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ከሂሳብ ቦርዱ የሚሰጥ ህጋዊ የምዝገባ የምስክር ወረቀት።
  2. ትክክለኛ የቲን እና የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት።
  3. በመንግሥታዊ/መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ኦዲት በማካሄድ ልምድ ያላቸው።
  4. ተዛማጅ የሙያ ማረጋገጫዎችን (CPA/ACCA) እና ቢያንስ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የባችለር ዲግሪ ያላቸው የኦዲት ባለሙያዎች CV።
  5. የቅርብ ጊዜ በመንግስታዊ/መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የኦዲት ስራ የሰሩበት የምስክርነት ደብዳቤዎች ያላቸው ቢሆኑ ተመራጭ ይሆናሉ።
  6. የቴክኒክ እና የፋይናንስ ፕሮፖዛሎችን አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ ማያያዝ።
  7. እያንዳንዱ ተጫራች የሚያቀርበውን ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ብቻ በድርጅቱ ስም አሰርቶ እስከ ሕዳር 11/2019 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ ከቴክኒካል (የህጋዊነት) ሰነዱ ውስጥ አብረው ማስገባት ይኖርበታል። ከሚያቀርበው ጥቅል ዋጋ 2% በታች /CPO/ የሚያቀርብ ለውድድሩ ብቁ አያደርግም።

ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን የዋጋ ሰነዶች ቴክኒካል ሰነድ (ህጋዊነት) እና ቴክኒካል ፕሮፖዛል እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ከዚያም ሁለቱ የታሸጉ ኤንቨሎፖች በአንድ ትልቅ የታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 11/2019 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባችኋል።

ተወዳዳሪዎች ስለጨረታው አፈፃፀም የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) አየር ጤና ከሚገኘው ዋናው ቢሮ በመግዛት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሞልተው ሊያስገቡ ይችላሉ።

ጨረታው የጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሕዳር 14/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይከፈታል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ: ተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት አየር ጤና፣ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት
የመ.ሳጥን ቁጥር 30153 ኢሜይል admin@hopeenterprises.org
ስልክ ቁጥር 0113694480/0113693871
አዲስ አበባ

ተስፋ ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Hope Enterprises, an Ethiopian NGO, seeks qualified audit firms for an investigative audit of its project financial statements for 2024 and 2025. Firms need a renewed licence, accounting board registration, TIN, VAT, NGO audit experience and CPA/ACCA-qualified staff.
Save Tender