Tender Detail

Tender Details

  • Company BRANNA PRINTING ENTERPRISE (ብራና ማተሚያ ድርጅት)
  • Address ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ላይ በስተግራ በኩል : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114 42 64 80
  • Website
  • Deadline24 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 1,000.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 2% (CPO ወይም Bank Guarantee)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከቀኑ 4:30 ሰዓት፣ በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ
  • Categories Building Construction

ብራና ማተሚያ ድርጅት የህንፃ ግንባታ ስራ

BRANNA PRINTING ENTERPRISE (ብራና ማተሚያ ድርጅት)


የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር :BM/NCB/CW/03/2019

የብራና ማተሚያ ድርጅት በሚያቀርበው የግንባታ ዲዛይን እና የቴክኒክ መስፈርት መሠረት የህንፃ ግንባታ ስራዎችን ህጋዊ በሆኑ ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ደረጃቸው GC/BC 1 እና 2 የሆኑ፣
  2. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የ 2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  3. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በብራና ማተሚያ ድርጅት ዋናው መሥሪያ ቤት፣ ቢሮ ቁጥር 26 በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ፋይናንሽያል ዶክመንት እና ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ አሽገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስተኛው (15ኛው) ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 26 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት አስራ አምስተኛው (15ኛው) ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓትተዘግቶ፣ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4:30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። (ቀኑ የሳምንቱ እረፍት ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል)።
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡
አድራሻ፡ ብራና ማተሚያ ድርጅት፣ አዲስ አበባ
የቢሮ ቁጥር፡ 26
ስልክ ቁጥር፡ +251-11-4421664
ዌብሳይት / ኢሜይል፡ branna.printing@gmail.com

የብራና ማተሚያ ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Branna Printing Enterprise in Addis Ababa invites GC/BC grade 1 and 2 contractors to bid for building construction works per its design and technical specifications. Open bid.
Save Tender