የሻሸመኔ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሞያሌ እና አርሲ ነጌሌ ደንበኞች አገልግሎት ማዕከል ቢሮ አጥር እና የጥበቃ ቤት ግንባታ
የሻሸመኔ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEU-SHR/NCB/001/2019
የሻሸመኔ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሻሸመኔ ከተማ ሪጅን ጽ/ቤት ስር የሚገኘውን ሞያሌ እና አርሲ ነጌሌ ደ/አ/ማዕከል ቢሮ አጥር እና የጥበቃ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
| ቁጥር | የሎት ቁጥር | የግንባታው ስራ የሚገኝበት ቦታ | የጨረታው ማስከበሪያ ብር | ጨረታው የሚዘጋበት ቀን እና ሰዓት | ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት |
| 1 | ሎት 1 | ሞያሌ ደ/አ/ማዕከል ቢሮ አጥር እና ጥበቃ ቤት | 465,000.00 (አራት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ብር) | ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም 8:00 ሰዓት | ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ይከፈታል። |
| 2 | ሎት 2 | አርሲ ነጌሌ ደ/አ/ማዕከል ቢሮ አጥር እና ጥበቃ ቤት | 330,000.00 (ሦስት መቶ ሰላሳ ሺህ ብር) | ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም 8:00 ሰዓት | ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም 8:30 ሰዓት ይከፈታል። |
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
- በደረጃ አምስት (5) እና ከዛ በላይ የግንባታ ተቋራጭ/BC&GC/ ያለው ሆኖ በዘርፉ ተዛማጅነት ያለው አንድ የመልካም ስራ አፈፃፀም፤የክፍያ ሰርተፍኬት እና ውል ማቅረብ የሚችል፣
- ከዚህ በፊት ከድርጅታችን ጋር ስራ ሰርተው በወቅቱ ያላስረከቡ ኮንትራክተሮች በዚህ ጨረታ መወዳደር አይችሉም::
- በገቢዎች አስተዳደር ባለስልጣን በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ያለው እና ደብዳቤውን ማቅረብ የሚችል፣
- የጨረታ ሠነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሻሸመኔ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ጽ/ቤት ሻሸመኔ ከተማ ሞቢል ሰፈር ሀይሌ ሆቴል ጎን በሚገኘው ህንፃ የሪጅኑ ሰፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 በመቅረብ የማይመለስ ብር 2000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሻሸመኔ ሪጅን በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000256449033 በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር ለሎት 1. 465,000.00 (አራት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ብር) ለሎት 2. 330,000.00 (ሶስት መቶ ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ከና ኦርጅናል በማለት እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም 8:00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል::
- ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0913920255 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ::
የሻሸመኔ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Utility Shashemene Region seeks BC/GC Grade 5 or above contractors to build office compound fences and guard houses at its Moyale and Arsi Negele customer service centres, in 2 lots. Open bid.
