Tender Detail

Tender Details

  • Company ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline25 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500 ብር (የማይመለስ)
  • Bid Security200,000 ብር (CPO ወይም ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዛው እለት 8:30
  • Categories Ict Equipment'S And Its Accessories , Electronics Materials

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ የተሽከርካሪ GPS መከታተያ እና የነዳጅ መጠን መቆጣጠሪያ (Fuel Level Sensor) መሳሪያ ግዥና ገጠማ

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/02/2019

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ ላሉት ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች የአቅጣጫ ማመላከቻ መቆጣጠሪያ እና የነዳጅ አጠቃቀም መቆጣጠሪያ መሳሪያ (GPS Vehicle Tracking System and Fuel Level Sensor) ማሰራት ይፈልጋል:: ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

  1. በዘርፉ የተሰማሩ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና ሌሎች አስፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:00 በመምጣት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ::
  3. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ከብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል::
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የሰያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው::
  5. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል::
  6. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይችልም::
  7. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም::
  8. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለውም::
  9. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል::
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8:30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል::
  11. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል::
  12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ - ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-25-19

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Geda Transport and Logistics S.C. seeks bidders to install a GPS vehicle tracking system and fuel level sensors on its dry cargo trucks. Bidders submit separate financial and technical offers, original and copy. Open bid.
Save Tender