Tender Detail

Tender Details

  • Company Fire and Disaster Risk Management Commission (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን)
  • Address አዲስ አበባ ቅ/ጊዮርጊስ ፊት ለፊት በሚገኝ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 1ኛ ፎቅ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 41 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-878-76-86
  • Websitehttps://edrmc.gov.et/
  • Deadline20 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት ብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ሎት ብር 5,000 (CPO)
  • opening dateበዚያው እለት ከረፋዱ 4:30፣ በቅርንጫፉ አዳራሽ
  • Categories Printing And Publishing , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ ህትመት፣ የጽዳት ዕቃዎች እና ሌሎች እቃዎች ግዥ

Fire and Disaster Risk Management Commission (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን)


የጨረታ ማስታወቂያ

በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2019 በጀት የአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ፣ ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን ፣ ሎት 2 ህትመት ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች ሎት 4 [...] የቢሮ መገልገያዎች እና ሎት 5 [...] ልብሶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል :: በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባችኋል::

  1. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ
  2. በመስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ እና የግብር መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ::
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
  4. ተጫራቾች ከወሰዱት የጨረታ ሰነድ ዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ በሌላ ቅፅ ቢያቀርቡ ተቀባይነት አይኖረውም::
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
  6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ::
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፤ በ11ኛው ቀን እስከ አራት ሰአት ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው 11ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከረፋዱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፉ አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል::
  8. በጨረታው ለመሳተፍ ከሎት1 - 5 ላለው ለእያንዳንዱ ሎት 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማሲያዝ አለባቸው ::
  9. ዘግይተው የቀረቡ የመወዳደሪያ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም::
  10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል::
  11. በጨረታው ተወዳድሮ ያሸነፈውን እቃ በቅርጫፉ ጥራት /ቴክኒክ ኮሚቴው ጥራቱ ሲረጋገጥ ተጫራቹ በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ በቅርጫፉ ንብረት ክፍል ማድረግ ይኖርበታል ::
  12. ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ ቢያንስ ለ60 ቀናት መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል ::
  13. ቅርጫፉ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20 በመቶ ለመቀነስ ወይም የሚገዛውን እቃ ወይም አገልግሎት ብዛት /መጠን ለመጨመር መብት ይኖረዋል::
  14. በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
  15. ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ወይም መረጃ ማግኘት ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር:-0116-68-47-97 /0116- 66-81-73 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ::

አድራሻ :- ከማዕድን ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ ዩድ አቢሲኒያ ኢተርናሽናል ሆቴል አጠገብ በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 01-16-68-47-97

በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅንርጫፍ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Fire and Disaster Risk Management Commission, Yeka Branch, seeks suppliers in 5 lots, including stationery, printing services and cleaning items. Samples required where specified. Open bid.
Save Tender