ካፋ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ዩኒየን የሂሳብ አሰራር ሶፍትዌር ማበልጸግ እና ማስጀመር
ካፋ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ ኅብረት ሥራ ዩኒየን
የጨረታ ማስታወቂያ
ካፋ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ ኅብረት ሥራ ዩኒየን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የሚገኘው ዩኒዬን በዞን ውስጥ ከሚገኙ ዩኒዬኖች አንዱ ሲሆን በ2019 በጀት ዓመት የሂሳብ አሰራር በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆንና ድጂታላይዝ ለማድረግ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ ዩኒዬኑ ባለው ሰርቨር ላይ ሶፍት ዌር ማስበልጸግ ይፈልጋል:: ስለሆነም ሶፍት ዌሩን በማበልጸግና የተለያዩ የቁጠባ አይነቶች፣ የብድር አይነቶች፣ አነስተኛ የብድር ኢንሹራንስ አገልግሎት፣ የሰው ኃይል አስተዳደርና ቅርንጫፍ አገልግሎት ያካተቱ መረጃዎችን በማስገባት በዘርፉ ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና በመስጠት አገልግሎት ማስጀመር የሚችል ማንኛውም ህጋዊ አቅራቢ መወዳደር ይችላል::
በዚህ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው:-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
- ቫት ተመዝጋቢ የሆነና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው ወይም /supplier list/ ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ስለመሆኑ ማቅረብ የሚችል፤
- ከዘመኑ ግብር ዕዳ ነጻ የሆነ፤
- ባለፉት 4 ተከታታይ ዓመታት በአንዱ ማለትም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በአንዱ በተመሳሳይ ተቋማት ማለትም ገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ዩኒዬኖች ወይም የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት መስራቱን የሚያረጋግጥ መልካም የሥራ አፈጻጸም መቅረብ የሚችል፤
- በኢንሳ /Ethiopia cyber security/ የተረጋገጠና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- ማንኛውም CPO ብር 50000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ የሚችልና መስፈርቱን የሚያሟላ ተጫራች የማይመለስ ብር 500 በአካውንት ቁጥር 1000029085262 ገቢ በማድረግ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ 03 ቀበሌ ቦንጋ መምህራን ት/ት ኮሌጅ ፊት ለፊት በሚገኘው በዩኒዬኑ ጽ/ቤት ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ዶክመንት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ በማሸግና በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በዕለቱ 4:30 የሚከፈት ይሆናል:: ጨረታ መዝጊያና መከፈቻ ቀን በመንግስት ሥራ ሰዓት ካልሆነ በቀጣይ ሥራ ሰዓት የሚሸጋገር ይሆናል::
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ:- 0473310583/0917866360/0912132382/0902508326 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
ካፋ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ ኅብረት ሥራ ዩኒየን
✨ messages.ai_summary
Kafa Saving and Credit Cooperative Union (Bonga, Kafa Zone) seeks a supplier to develop and deploy accounting software on its server covering savings, loans, micro-insurance, HR and branch services, with staff training. INSA certification required. Open bid.
