የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ለተፈጥሮ ኃብት መሬት አጠቃቀም እና ለአትክልትና ፍራፍሬ ዳይሬክቶሬቶች አገልግሎት የሚውሉ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ፣ የቡናና ፍራፍሬ ፕላስቲክ፣ የእጅ ጋሪ፣ የውሃ ማጠጫ እና ከብረት የተሰሩ የእርሻ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ ያወዳድሮ ይገዛል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለተፈጥሮ ኃብት መሬት አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት እና ለአትክልትና ፍራፍሬ ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል በፓኬጅ አንድ ስር ለተቀመጠው ሎት 01 የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 10 ሎት 02 የቡናና ፍራፍሬ ፕላስቲክ ባለ14 እና ሎት 3 ባለ 20 በፓኬጅ ሁለት ስር ሎት 1 የእጅ ጋሪ ውሃ ልክ 1 የውሃ ማጠጫ ጆሮዲን እና ሎት 02 የእርሻ መሳሪያ ከብረት የተሰራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ መታደሱን የሚገልፅ ንግድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ወይም በኢጂፒ የተመዘገ
- የግዥው መጠን ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማደረግ ከኦርጅናል ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ፣ጆርዲን፣የእጅ ጋሪ እና የእርሻ መሳሪያ ግዥ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 21 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ ብር በቁርጥ ለሎት 01 ለባለ10 ፕላስቲክ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ለሎት.02. ለባለ 14 ፕላስቲክ 400,000.00/አራት መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለሎት 03 ለባለ 20 ፕላስቲክ ብር 400,000.00/አራት መቶ ሺህ ብር እንዲሁም በፓኬጅ 02 ስር ለሎት 01 የእርሻ መሳሪያ ብር 100,000 አንድ መቶ ሺ. ብር እና ሎት 02 እርሻ መሳሪያ ከብረት ለተሰሩ ብር 50,000/አምሳ ሺህ ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነዱን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ ማስከበሪያውን ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናንሻል ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 027 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 11ኛ ቀን ቅዳሜ ና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4:00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 27 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 2205849/0583208095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል። ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት።
- በፓኬጅ 1/አንድ/ ስር ለተቀመጡት ሎቶች ማንኛውም ተወዳዳሪ ዋጋ መስጠት ወይም መወዳደር የሚችለው ለአንድ ሎት ብቻ ሲሆን ከአንድ በላይ ሎት ሞልቶ የተገኘ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ
✨ messages.ai_summary
Amhara Agriculture Bureau buys by open tender: seedling nursery plastic bags in three sizes (package 1, one lot per bidder), and hand carts, watering cans and steel farm tools (package 2). Bidders need a renewed sector trade licence, tax clearance, TIN and supplier registration.
