Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline07 Dec 2026, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ 1/4 (C.P.O በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ፣ የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የሚገኝ ቤትና ይዞታ የሐራጅ ሽያጭ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለሙብት እነ ሂሩት አበበ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ብሩክ ጌታቸው መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/105552 በ25/10/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/107523 በ27/11/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የቤት ቁ/692 የካርታ ቁጥር 4/31/53/00 እና በእነ አቶ ጌታቸው አበበ ወልዴ የተመዘገበ ቤት እና ይዞታ የቦታ ስፋት 89 ካ/ሜ የውስጥ ለውጥ መንገድ 17 ካ/ሜ ይነካዋል፤ ይዞታው ጉቶሜዳ (LOCAL DEVELOPMENT PLAN) ጥናት ውስጥ የሚገኝ ካርታ ያለው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 2,889,346 ( ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺህ ሶስት መቶ አርባ ስድስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 28 ቀን 2019ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል::

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለሙብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለሙብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Federal Courts Judgment Execution Office auctions, by court order, a titled house and 89 m² plot (house no. 692) in Gullele sub-city, Woreda 4, Addis Ababa, within the Gutomeda local development plan area. The buyer pays transaction tax. Public auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender