በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 11 ፋይናንስ ፅ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተደረጁ እቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በኮልፌ ቀራኒዮ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 11 ፋይናንስ ፅ/ቤት
የ2019 በጀት አመት የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 11 ፋይናንስ ፅ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተደረጁ እቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
| ሎት1 | የሰራተኛመዝናኛ ክበብ |
| ሎት2 | ዶሮ እና የዶሮ ኬጅ |
| ሎት3 | የዕድሳት ጥገና እቃዎች |
በመሆኑም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 (ስስት መቶ ብር) በመክፈል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ካራ ቆሬ ወታደር ሰፈር የሚገኘው ህንፃ ቀርበው መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን::
ተጫራቾች ማሟላት የሚኖርባቸው:-
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከብያ (ለሎት1፤2፤3፤(10000/አስር ሺህ) በባንክ በተረጋጠ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸዉ::
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ ከተደራጁ ሲፒኦ ማስየዝ አይጠበቅባቸዉም በምትኩ በኃላፊ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸዉ::
- የሚቀርበዉ የዋጋ ሰነድ ለቫት ተጠቃሚዎች ቫትን ያካተተ መሆን አለበት::
- ማንኛዉም ተጫራች የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ማህተም ስልክ እና ፊርማ መኖር አለበት::
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ኮፒ እና ዋናውን በተለያየ ፖስታ በየሎቱ ለይቶ ማቅረብ ይኖርበታል::
- ለሎት 1፤2፤3 ደረሰኞቻቸው ኪው አር ኮድ ያለው መሆን አለበት ::
- ለሎት 1 ከቫት ነፃ ከሆኑ ነፃ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖሩበቸዋል ::
- አሸናፊ ተጫራች በሰነድ ዉስጥ በተመለከተዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ቀርቦ ዉል መዋዋል አለባቸዉ::
- ተቋሙ እቃዎቹን በፈለገው ሰዓት ብዛቱን እንዲያቀርብ ማዘዝ ይችላል
- የእቃ ማስረከቢያ ቦታ ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 11 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ይሆናል::
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ለተወዳደሩበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው:: ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድር ውጪ ይሆናል:: እቃው በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይደረጋል::
- ለዶሮ እና ለኬጅ እቃዎች ሳምፕል ሙሉ ዝርዝር የሚገልፅ በፎቶ ማቅረብ ይችላሉ
- ለሰራተኛ መዝናኛ በሶሻል ኮሚቴ እየታየ አስተያየት የሚሰጥበት ይሆናል::
- የሰራተኛ መዝናኛ ዋጋው ጥቅል ላሸነፈው ነው የሚሰጠው::
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል::
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ ከተደራጁ ከሆነ በግዥ መመሪያ መሰረት በህግ አግባብ የሚጠየቁ ይሆናል ::
- በጨረታው ከቀረቡ የእቃ ዝርዝሮች ውስጥ ተቋሙ 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል ::
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ 10% በባንክ በተረጋጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ::
- አሸናፊ ድርጅት ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር ) ቀን ውስጥ እቃውን ማቅረብ ይኖርበታል::
- አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም::
- የጨረታው ሳጥን አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በአስራ አንደኛው ቀን(11) በ11/03/2019 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል::
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት እና ጉልበት ጫኝና አውራጅ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ግምጃ ቤት ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች (በጨረታው) የተሸነፉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይሆናል:: በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጽ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 11 ፋይናንስ ፅ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Kolfe Keranio Sub-city Woreda 11 Finance Office (Addis Ababa) seeks suppliers in 3 lots: staff recreation club service, chickens and poultry cages, and renovation materials. Bidders need a renewed licence, registration and TIN; MSEs may give a guarantee letter instead of CPO. Open bid.
