በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ለሚያስገነባው እና ለሚያሳድሰው የግንባታ ስራ በጥቃቅንና አነስተኛ ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 ማህበር እና ደረጃ 5 አማካሪ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል::
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት
የምክር አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አማ 001/2019 ዓ.ም
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ለሚያስገነባው እና ለሚያሳድሰው የግንባታ ስራ በጥቃቅንና አነስተኛ ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 ማህበር እና ደረጃ 5 አማካሪ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል:: በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ ደረጃቸው ከዚህ በታች በተጠቀሰው መስፈርት በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
| ሎት | የስራዉ አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና | ደረጃ | የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን | የጨረታ ማስገቢያ ቀን | የጨረታ መክፈቻ ቀን |
| ሎት 1 | ወ/ሮ ቀለመ ወርቅ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የአጥር እና ድጋፍ ግንብ ግንባታ ስራ | 20,000 ብር/ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ | በጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 2 | ወረዳ 02 እና ወረዳ 06 የድጋፍ ግንብ፣ የመጫወቻ ቦታ ግንባታ ፣ ላይብረሪ ግንባታ | 20,000 ብር/ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ | በጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 3 | የወረዳ 5 ወጣት ማዕከል ህንጻ እድሳት ፣ አጥር ግንባታ፣ የጥበቃ ቤት ግንባታ፣ ስቶር እና ሱቅ ስራ | 20,000 ብር/ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ | በጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 4 | ወረዳ 02 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ህንጻ እድሳት ስራ | 20,000 ብር/ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ | በጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 5 | የወረዳ 6 ወጣት ማዕከል ህንጻ እድሳት ስራ እና የጥበቃ ቤት ግንባታ | 20,000 ብር/ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ | በጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 6 | ወረዳ 06 አዳራሽ ጥገና | 20,000 ብር/ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ | በጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 7 | የወረዳ 04 የጥበብ እድገት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የስፖርት ሜዳ ግንባታ | 20,000 ብር/ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ | በጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 8 | አፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አጥር ግንባታ | 20,000 ብር/ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ | በጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 9 | ወረዳ 2 ጂ+4 ራስ አምባ ጤና ጣቢያ እድሳት | 20,000 ብር/ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ | በጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 10 | ወረዳ 2 ጂ+4 ራስ አምባ ሰርቶ ማሳያ ግንባታ | 50,000 ብር/ | ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 11 | ወረዳ 2 ጂ+4 ፖሊስ ካንፕ ግንባታ | 50,000 ብር/ | ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
አማካሪዎች ድርጅቶች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል::
- በዘርፉ የ2019 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- ማንኛውም አማካሪ ከፌደራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2:30 እስከ 10:00 ድረስ ከተራ ቁ.1-4 ላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናዉን(orginal) እና የማይመለስ ቅጂ(copy) ይዞ በመቅረብ ከሎት 1-9 በነጻ እና ከሎት 10-11 የማይመለስ 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ሠነዱን ከአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ::
- ማንኛውም ተጫራቾች ለ60 ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / BID BOND / በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ (UnConditional Bank Guarantee) ከላይ በተጠቀሰው እና በሚሳተፉበት ፕሮጀክት የብር መጠን ማቅረብ ግዴታ አለበት:: የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፤ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: በተጨማሪም የታሸገውን 6 ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል:: የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያስርዛል::
- ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን ፣ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኢንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 4:00 ማስገባት ይኖርባቸዋል:: የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል::
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት በአራዳ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ (Instruction to Bidder(ITB) and Scope of Consultancy service) እንዲያነቡ ይመከራል::
- አማካሪው ድርጅት የዲዛይን ማሻሻያ፣ የግንባታ ክትትል እና የውል ማስተዳደር ስራ ይሰራል::
- አማካሪ ድርጅቱ ስራውን በጥራት ለማከናወን የሚከተላቸውን መሰረታዊ ስራቴጂዎች የሚያቀርብ፤ እነዚህም ባለሙያዎቻቸው ተጠያቂ እንደሚያደርገው ማረጋገጫ የጸደቀ በስራ አስኪያጅ ወይም በኃላፊው የተፈረመ ሆኖ ማህተም ያለው ሰነድ የሚያቀርብ መሆን አለበት::
- አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁ ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት አለው::
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ አራት ኪሎ በሚገኘው በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በግንባር በመቅረብ መረዳት ይችላሉ::
አራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Arada Sub-city Design and Construction Works Office seeks consultants for design revision, construction supervision and contract administration of 11 building, renovation and fence lots in Addis Ababa. Lots 1-9 for grade 1 micro-enterprise consultants; lots 10-11 for grade 5 and above.
