Tender Detail

Tender Details

  • Company በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዳርማር ጫማ ፋብሪካ አጠገብ ወይም ከልደታ ፍርድ ቤት ጀርባ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118685799
  • Website
  • Deadline16 Nov 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityበሎት ከብር 3,000 እስከ 30,000 (CPO)
  • opening dateበማግስቱ ከጠዋቱ 4:30
  • Categories Cleaning & Janitorial , Printing And Publishing , Textile, Garment & Leather , Furniture , Stationery Materials , Electronics Materials

የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ የፅህፈትና የፅዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ እቃዎች፣ ህትመት እና የጥገና አገልግሎት ግዥ

በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019

በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች በሎቱ መሰረት፡-

ሎትየዕቃው ዓይነትየጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን
ሎት 1የደንብ ልብስ13,000
ሎት 2አላቂ የማስተማሪያ እና የፅህፈት መሳሪያዎች11,000
ሎት 3አላቂ የፅዳት እቃዎች8,000
ሎት 4የጥገና እቃዎች እና የስራ እቃዎች5,000
ሎት 5የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና (ኮምፒውተር እቃዎች)30,000
ሎት 6ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና4,000
ሎት 7ቋሚ እቃዎች18,000
ሎት 8የተለያዩ ህትመት የስራዎች3,000
ሎት 9የደንብ ልብስ ስፌት3,000

ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩትን ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። በዚህም መሰረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን፣ ታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው በመንግስት ግ/ን/አስተዳደር ኤጀንሲ ደህረ ገፅ ላይ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተርጋገጠ ሲፒዩ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 200 ብር በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ ት/ቤቱ ፋይናንስና ግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በት/ቤቱ ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚወደደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳዳቸው ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡30 ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል። የመከፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወደደሩባቸው ሎት 1፣ሎት 2፣ሎት 3፣ ሎት 4 ሎት 6፣ሎት 8 ፣ሎት 9 ላይ ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 5 እና ለሎት 7 በቀረቡ የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  8. የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥው ፈፃሚ መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ እና ጥያቄ፤ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዳርማር ጫማ ፋብሪካ አጠገብ ወይም ከልደታ ፍርድ ቤት ጀርባ ደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 0118685799 ወይም 0118964301 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Dejazmach Balcha Abanefso Secondary School (Lideta Sub-city) seeks suppliers in nine lots: uniforms and tailoring, teaching and stationery supplies, cleaning items, maintenance items, electronics and computers, photocopier repair, fixed items and printing. Open bid.
Save Tender