የጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማ የቁፋሮ ቢቶችና ሲሊንደር እና የውሃ ጉድጓድ (Borehole) ካሜራ ግዥ
Tis Isat Water Works PLC (የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች የቁፋሮ ቢቶች እና ሲሊንደር እንዲሁም የውሃ ጉድጓድ (Borehole) ካሜራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
| ሎት | የእቃው አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ | የማቅረቢያ ቀን |
| ሎት 1 | የቁፋሮ ቢቶች እና ሲሊንደር | 200,000.00 | ከ30-45 ቀን |
| ሎት 2 | የውሃ ጉድጓድ (Borehole) ካሜራ | 100,000.00 | ከ30-45 ቀን |
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ።
የተጫራቾች መመሪያ፤
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባሕርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቱዴ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በC.P.O ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው።
- ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PR-03/2017 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል።
- ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሑፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሠራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
- የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት። የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት።
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ባሕር ዳር ከተማ የኩባንያው ጽ/ቤት መሆን አለበት።
- ማሳሰቢያ፡- አንድ ኩባንያችን ፍላሳት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሲሆን ይችላል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-48-26/058-320-25-48/ በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 መጠየቅ ይችላሉ።
ጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
✨ messages.ai_summary
Tis Isat Water Works PLC (Bahir Dar) seeks suppliers of drilling bits and cylinders (Lot 1) and a borehole camera (Lot 2), delivered to its Bahir Dar office. Open to licensed suppliers with VAT and TIN registration.
