Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ
  • Address ለገሀር አሮጌ ባቡር ጣቢያ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን 4ኛ ክፍለ ጦር አካባቢ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በማስተባበሪያ ጽ/ቤት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910147760
  • Website
  • Deadline16 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት ብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ሎት ብር 5,000 (CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateበ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት
  • Categories Textile, Garment & Leather , Safety Clothe And Shoes

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ (አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ) ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የጥበቃ ሠራተኞች ጫማ እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ


የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስፋ/ግጨ/046/2019

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ (አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ) ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የጥበቃ ሠራተኞች ጫማ እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የጥበቃ ሠራተኞች የስራ ጫማ(Leather shoe long boots)
  • ሎት 2 :የጥበቃ ሠራተኞች የስራ የደንብ ልብስ( Trawthers and shirt)

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ አካላት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ኛው ቀናት ድረስ ለገሀር አሮጌ ባቡር ጣቢያ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን 4ኛ ክፍለ ጦር አካባቢ የሚገኘው አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርበው ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. ቫት ተመዝጋቢ የሆነና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin.No) ያላቸው በሚወዳደሩበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በመንግስት መ/ቤት ግዢ ለመወዳደር እንደሚችሉ ከገቢ ሰብሳቢ ድርጅቶች ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው ላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ለእያንዳንዱ ሎት 5000 (አምስት ሺህ ብር) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የሚጫረቱበትን ዋጋ በእያንዳንዱ በጨረታ ሰነድ መሠረት እስከ 16 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል።
  4. ጨረታው በሁለት የታሸገ ፖስታ መቅረብ ያለበት ሲሆን በቴክኒካል ፖስታ አስፈላጊ ሰነዶች ትክክለኛ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ አብሮ መቅረብ አለበት።
  5. ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል
  6. ጨረታው በ16 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ሊገኙ ፈቃደኛ በሆኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ነገሮች ማሻሻል ወይም መተው አይችልም።
  8. የጨረታው ተሳታፊዎች አቅራቢዎች ከዚህ በላይ የተገለጹትን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለፋብሪካው ገቢ ሆኖ ተጫራቹ ከጨረታው ይሰረዛል።
  9. ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ ለገሀር አሮጌ ባቡር ጣቢያ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን 4ኛ ክፍለ ጦር አካባቢ የሚገኘው አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 09-13-99-43-49 ወይም 09-73-42-13-43 በመደወል ወይም ዘወትር በስራ ሰዓት በግንባር በመቅረብ ማነጋገር ይችላሉ።
  10. ማስረከቢያ ቦታ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ። ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ

✨ messages.ai_summary
Arjo Dedessa Sugar Factory (Sugar Industry Group) seeks suppliers of leather long boots (Lot 1) and work uniforms, trousers and shirts (Lot 2), for its security staff. Open to VAT-registered suppliers with a renewed trade licence and TIN. Open competitive bid.
Save Tender