ያገለገሉ የብረትና የእንጨት ጠረጴዛዎችና ሼልፎች፣ ጣውላና ብረት፣ ፋይል ካቢኔቶች፣ በሮች፣ ተሽከርካሪ ዲስፕለይና ሚዛን ሽያጭ (ሜማ/12/2/19) - ሜጋ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
Mega printing plc (ሜጋ ማተሚያ ኃ. የተ. የግ. ማህበር )
የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር ሜማ/12/2/19
ኩባንያችን ሜጋ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ የብረት ጠረጴዛዎችና ሼልፎች ፣ የእንጨት ጠረጴዛዎችና ሼልፎች ፣ የተለያየ ጣውላና ብረት ፣ የተለያዩ ፋይል ካቢኔቶች ፣ የተለያዩ በሮች ፣ ተሽከርካሪ ዲስፕለይ ፣ ሚዛን ወዘተ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ሜጋ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች እቃውን በአካል በመቅረብ ገርጂ ሜታ አካባቢ በሚገኘው የድርጅታችን መጋዝን በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 2/3/2019 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ለዚሁ ተብሎ በሜጋ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 217 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው ፡፡
- አንድ ተጫራች መግዛት የሚፈልገውን ከአንድ በላይ የእቃ ምድብ ከሆነ ለሚጫረተው ለእያንዳንዱ የእቃ ምድብ ዋጋ መጥቀስ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የእቃ ምድብ የሚጫረቱበት አጠቃላይ ዋጋ አስር በመቶ በሜጋ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ / ሲ.ፒ.ኦ/ የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ጨረታውን ላላሸነፉት ብቻ የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ይመለስላቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ/ዎች ቀሪውን ገንዘብ በአምስት /5/ የሥራ ቀናት ውስጥ አጠቃለው ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ከፍለው ንብረቱን የማያነሱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅታችን ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡
- ጨረታው በ2-3-2019ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ2/3/2019ዓ.ም ልክ ከቀኑ 7:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሜጋ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች አለመገኘት ጨረውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሕጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ ሜጋ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢ.ሮ ቁጥር 217
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913729631
ሜጋ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
✨ messages.ai_summary
Mega Printing plc is selling used steel and wooden tables and shelves, assorted timber and metal, file cabinets, doors, a vehicle display and a weighing scale. Any company or individual may bid; bidders must quote a price for each item category they want and may inspect the items at the company store in Gerji Meta.
