Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopiaq, Phone: +251112730852
  • Website
  • Deadline13 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 1/4 (ብር 422,075.25) C.P.O
  • opening dateህዳር 4 ቀን 2019 ዓ/ም ምዝገባው እንደተጠናቀቀ
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

የኮሮላ ተሽከርካሪ (ኮድ 3-B42849) የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ፊሽን ገረመው እና በፍ/ባለዕዳ ከንፈ ታደለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/13204 በ3/10/2018ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/22654 በ8/11/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ የሚገኝ የሰ/ቁ.ኮድ 3-B42849 ኢ.አ ኮሮላ ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,688,301 ( አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማንያ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ አንድ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 4 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A Toyota Corolla vehicle (code 3-B42849) is being sold at auction by the Federal Courts' Execution Office. Bidders must deposit 1/4 of the starting estimate as a certified CPO; bids above or below that amount are disqualified. The winner must deposit the full amount within 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender