Tender Detail

Tender Details

  • Company የሐረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን
  • Address ሐረር ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910415925
  • Website
  • Deadline05 Nov 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 1,500 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየቦታ ስፋት × መነሻ ዋጋ 5% (CPO ብቻ)
  • opening dateጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የአስረኛ ዙር የበድሪ በሪ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት የሊዝ ጨረታ (95 ፓርሴሎች) - የሐረሪ ክልል የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን

የሐረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን


የአስረኛ ዙር የበድሪ በሪ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት የጨረታ ማስታወቂያ

በከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 (ሀ - ሠ) መሠረት የወጣ

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን፣ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከተራ ፊደል (ሀ) እስከ (ሠ) በተዘረዘረው መሠረት፤ በሐረር ከተማ ጀጎል በድሪ በሪ አካባቢ በሚገኘው ቦታ ለመኖሪያ በአስራ አንድ (11) ብሎኮች የተዘጋጁ ስልሳ ሦስት (63) ፓርሴሎች እና ለንግድ መደብሮች የሚውሉ በስድስት (6) ብሎኮች ሰላሳ አንድ (31) ፓርሴሎች፤ እንዲሁም አንድ (1) ለካፌ ንግድ አገልግሎት የሚውል፤ በጠቅላላው ዘጠና አምስት (95) ፓርሴሎች የተዘጋጁ ይዞታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

የይዞታው አገልግሎት (Land Use)የብሎክ ብዛት (Blocks)የፓርሰል ብዛት (Parcels)
ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ (Residential)11 ብሎኮች63 ፓርሰሎች
ለንግድ መደብሮች የሚውሉ (Commercial)6 ብሎኮች31 ፓርሰሎች
ለካፌ ንግድ አገልግሎት የሚውል (Caf )—1 ፓርሰል
ጠቅላላ ድምር (Total Allocation)17 ብሎኮች95 ፓርሰሎች

የተጫራቾች መመሪያ እና የመወዳደሪያ መስፈርቶች

  1. የሰነድ ሽያጭ:- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተወዳዳሪ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን እሮብ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላል። ክፍያውን በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባዘጋጀው የኦንላይን ፖርታል (Harari Land Lease Tender Portal) በድረ-ገፅ https://sltms.hararsmartlandsystem.gov.et በመግባት ማከናወን ይቻላል። ለዚህም 1,500 ብሩን በሐረር ከተማ በሚገኝ ማንኛውም ባንክ ለጨረታ ሰነድ ሽያጭ በተዘጋጀው አካውንት ቁጥር 1000017606364 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ኦንላይን ፖርታሉ ላይ ስካን አድርጎ በማያያዝ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
  2. አማራጭ የሰነድ ግዢ አገልግሎት:- የኦንላይን ፖርታሉን አጠቃቀም ለሚቸገሩ ተጫራቾች አማራጭ የግዢ ማዕከላትን ያዘጋጀን ሲሆን፤ ተጫራቾች በአካል በመቅረብ በመሶብ 1 ማዕከል እንዲሁም በዋናው መሥሪያ ቤታችን ምድር ቤት ቢሮ ቁጥር 49 በመገኘት የጨረታ ሰነዱን በቀላሉ መግዛት ይችላሉ።
  3. የሰነድ ማስገቢያ ጊዜና የመጨረሻ ቀን:- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል። ለቦታዎች በካሬ ሜትር የሚያቀርቡትን ዋጋ እና የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድመ ክፍያ በጨረታ መወዳደሪያ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት፣ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የሰነድ ማስገቢያው የመጨረሻ ጊዜ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው።
  4. የሳጥን መዝጊያና መክፈቻ:- የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተዘግቶ፤ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አራተኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO):- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ቦታ የጠቅላላው የቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 5% (አምስት ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (በCPO ብቻ) በጥቅል ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. የቅድመ ክፍያ መጠን:- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ቅድመ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የሊዝ ዋጋ ከ20% (ከሃያ ፐርሰንት) ማነስ የለበትም።
  7. የግምገማ ነጥብ አሰጣጥ:- የተጫራቾች አሸናፊነት የሚለየው ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ዋጋ 80% (ሰማንያ ፐርሰንት) እና የቅድመ ክፍያ መጠን 20% (ሃያ ፐርሰንት) ተምር ውጤት ተሰልቶ በሚገኘው ከፍተኛ ነጥብ መሠረት ይሆናል።
  8. የCPO ተመላሽ:- የጨረታው አሸናፊዎች ተለይተው በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በይፋ ከተገለጹ በኋላ፤ በጨረታው ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  9. ለተጨማሪ መረጃ:- በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ይፋዊ ድረ-ገፅ https://hudco.gov.et በመግባት ወይም በአካል ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።
  10. ማሳሰቢያ:- ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን

✨ messages.ai_summary
Harari Region Land Development & Management Authority invites bids for lease of 95 parcels in Harar's Bedri Beri redevelopment: 63 residential (11 blocks), 31 commercial shops (6 blocks), and 1 café parcel. Bidders must submit lease price per m² and a down payment of at least 20% of total lease value.
Save Tender