የመጀመሪያ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ (4455.5 ካ.ሜ ለድርጅትና ለመኖሪያ) - የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
የመጀመሪያ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጨፋ ሮ/ከ/አስተዳደር የጨፋ ሮቢት ከተማና መ/ል/ፅ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ 1647.5ካሬ የድርጅት እና 2258 ካሬ መኖሪያ በጠቅላላ ስፋታቸው 4455.5 ካሬ ሜትር የሆኑ ለድርጅት እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች -
- የጨረታውን ሰነድ በጨፋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ፅ/ቤት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢ.ትዮ. ብር 1000.00 /አንድ ሺ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን / Specifection/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 30 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ10 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል፡፡
- ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በኦ/ብ/ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ፅ/ቤት በመሬት ልማትና ባንክ ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ 12/ 02 /2019 እስከ25/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ 25 / 02 /2019ዓ.ም 11:30 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ26/ 02/2019 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት የጨፋሮቢት ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኚዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
- የአካባቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በጨፋሮቢት ከተማ አስተዳደር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ -- በስልክ ቁጥሮች /+251920480605/ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የጨፋሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት
✨ messages.ai_summary
The Chefa Robit Town Administration invites bids for a lease of 4,455.5 sq m of urban land in Chefa Robit — 1,647.5 sq m for enterprise and 2,258 sq m for residential use. Bidders must meet the specification in the bid document and submit a CPO bid security of at least 30% of the lease base price.
