Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopiaq, Phone: +251112730852
  • Website
  • Deadline24 Nov 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 1/4 (ብር 581,278.25) C.P.O
  • opening dateህዳር 15 ቀን 2019 ዓ/ም ምዝገባው እንደተጠናቀቀ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሻሌ ሳይት ብሎክ 26 የሚገኝ 59.07 ካ.ሜ የንግድ ቤት የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍባለመብት ሳምሶን ጉሉማ እና በፍ/ባለዕዳ መስፍን ታደሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/212091 በ1/8/2018ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/216282 በ29/10/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በሻሌ ሳይት ብሎክ 26 የሚገኝ የካርታ ቁጥር ለ/ኩ/18/8/3/162568/00 በፍ/ባለዕዳ ስም የተመዘገበ ቤት የሴሪያል ቁጥር 1682364 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 59.07 ካ/ሜ የቤቱ አገልግሎት በካርታቸው መሰረት የንግድ ቤት የሆነ ቤቱ የንግድ ቤት ስለሆነ በገቢዎች ቢሮ መመሪያ መሰረት ካፒታል ጌይን የሚከፈል የሆነ የሀራጅ መነሻ ዋጋ 2,325,113 (ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ አስራ ሶስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል ካፒታል ጌን ግብር ቀኙ የሚከፍሉ መሆኑ ታውቆ ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A 59.07 sq.m commercial building (Block 26, Shale Site, Bolemi Kura) is being sold by auction through the Federal Courts' Execution Office. Buyers pay capital gains tax; bidders must deposit 1/4 of the estimate via CPO.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender