ፀሐይ ሁለገብ የገ/ኅ/ሥ/ማህበራት ዩኒየን – የምግብ ዘይት ፋብሪካ ማስፋፊያና ከተለያዩ የቅባት ሰብሎች ዘይት ለማምረት የአዋጭነት ጥናት አገልግሎት ግዥ
ፀሐይ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ኃ/የተ/.
የአዋጭነት ጥናት ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ፀሐይ ሁለገብ የገ/ኅ/ሥ/ማህበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ አዘዞ አየር ማረፊያ አካባቢ የሚገኘው በዩኒየኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ገንብቶ የምግብ ዘይት እና ፋጉሎ በማምረት የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ ያለ መሆኑ ይታወቃል::ስለሆነም አሁን እያመረተ ከሚገኘው የኑግ ዘይት በተጨማሪ ከሌሎች የቅባት ሰብሎች የምግብ ዘይት ለማምረት እና ፋብሪካውን ለማስፋፋት የአዋጭነት ጥናት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠናት ይፈልጋል::
ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ጨረታውን መጫረት የምትችሉ በመሆኑ:-
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላችሁ እና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ::
- ባርኮድ/QR CODE/ ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል::
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና ሌሎችንም መረጃዎች ዋናውን እና ኮፒውን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ሲኖርባቸው አሸናፊ ላልሆኑ ተጫራቾች አስይዘውት የነበረውን ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::
- አሸናፊው አካል የውል ማስከበሪያ 10% በሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርበታል::
- የጨረታ ሰነዱ ከፀሐይ ሁለ/የገ/ኅ/ሥ/ማህበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ በፖስታ በማሸግ አዘዞ አየር ማረፊያ አካባቢ በሚገኘው ከፀሐይ ሁለገብ የገበሬወች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ጽ/ቤት ውስጥ ከ10/02/2019 እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል::
- ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251918350961/+251966679255 ይደውሉ::
ፀሐይ ሁለገብ የገ/ኅ/ሥ/ ማህበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ
✨ messages.ai_summary
Tsehay Multipurpose Farmers' Cooperative Union seeks a consultancy to conduct a feasibility study for expanding its edible oil factory and producing oil from various oilseed crops beyond current niger seed oil. Eligible bidders need a valid sector license, tax compliance, and a barcoded/QR receipt.
