Tender Detail

Tender Details

  • Company DASHEN BANK S.C (ዳሽን ባንክ አ.ማ)
  • Address ብሔራዊ ባንክ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 5-18-03-56
  • Websitehttps://dashenbanksc.com/
  • Deadline23 Oct 2026, 12:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ዓይነት ምድብ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 20 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ
  • opening dateበዚያው ቀን በ09:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  • Categories Office And Home Furniture , Office Machines And Computers , Office Equipment

ዳሽን ባንክ አ.ማ. በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለሁለተኛ ዙር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

DASHEN BANK S.C (ዳሽን ባንክ አ.ማ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የተለያዩ ቋሚ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ ሽያጭ DB/052/2019

ዳሽን ባንክ አ.ማ. በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለሁለተኛ ዙር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ቂራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል በመምጣት የጨረታውን መረጃ ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
  2. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከቀኑ 8:00 እስከ 10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በባንኩ መጋዘኖችና ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዓይነት ምድብ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 20 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲ.ፒ.ኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው።
  5. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላሲያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
  6. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከዳሽን ባንክ አ.ማ. ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣ ሆኖም በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ክፍያ በቶሎ ገቢ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ ክፍያው በዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች በተዘጋጀ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በ 5 ኛው ቀን ማለትም ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓም ከቀኑ በ06:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ09:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
  8. በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ3 /ሶስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 2 /ሁለት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከባንኩ ጋር ውል መፈራረምና ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ከላይ በተገለጸው መሰረት ውል ካልፈረሙ ወይም ሙሉክፍያውን በተጠቀሰው ግዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
  9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ንብረት በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ ውል በፈረሙ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ በማንሳት ማጠናቀቃቸው ሲረጋገጥ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  10. ባንኩ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ያደረጋል።
  11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-4655552 ወይም 011-4706065 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
  12. ባንኩ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

ዳሽን ባንክ አ.ማ.
አዲስ አበባ

ተ.ቁየእቃው አይነትመለኪያብዛት
1ADDING MACHINEበቁጥር3
2ELECTRICAL TYPEWRITERበቁጥር1
3QUEUING MANAGEMENT SYSTEMበቁጥር2
4SWICHበቁጥር26
5Monitor/ System unitበቁጥር71
6METAL DETECTORበቁጥር60
7Kama Small Generatorበቁጥር4
8LOST AND FOUND DISPLAY BOARDበጥቅልበጥቅል
9NOTICE BOARDበጥቅልበጥቅል
10WALL CLOCKበቁጥር4
11EPSON TERMAL PRINTERበቁጥር35
12TALLY PRINTERበቁጥር12
13NOTE COUNTING MACHINE FOR CASHERበቁጥር15
14NOTE COUNTING MACHINE FOR TELLERበቁጥር17
15MANAGERIAL TABLEበጥቅልበጥቅል
16COMPUTER STAND TABLEበጥቅልበጥቅል
17HIGH BACK SWIVEL CHAIRበጥቅልበጥቅል
18STORAGE CABINETበጥቅልበጥቅል
19LOW BACK SWIVEL CHAIRበጥቅልበጥቅል
20GUEST CHAIRበጥቅልበጥቅል
✨ messages.ai_summary
Dashen Bank invites bids for the second-round sale of used fixed assets (furniture, office machines, computers, equipment) in their current condition and location. Bidders must buy the tender document, submit a 20% CPO bid security, and meet document requirements; incomplete bids are rejected.
Save Tender