የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት የኤሌክትሪክ ሞተር ሣይክል፣ ፈርኒቸር፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ ሕትመት፣ የእንስሣት መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጋሞ ዞን ፋይናንስና ኘላን ልማት መምሪያ አ/ምንጭ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ፣
የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት 1/ የኤሌክትሪክ ሞተር ሣይክል 2/ ፈርኒቸር 3/ የሞተር ሣይክል ጎማ 4/ የግንባታ ዕቃዎች 5/ ሕትመት 6/ ናይትሮጅን ጃር 7/ የኖራ ውሀድ ከነትራንስፖርት 8/የእንስሣት መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ 9/ የፖሊቲን ቲውብ/ ፕላስቲክ ባግ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና በአቅራቢነት የተመዘገቡ
- የንግድ ፍቃድና ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15 ባሉት ቀናት ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000038613263 በማስገባት እና የባንክ አድቫይስ ይዘው ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ደረሰኙን በማሳየት ከጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ(BiD security) ለእያንዳንዱ 80,000/ሰማኒያ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በዋናው የሕጋዊነት ሰነድ እንቬሎፕ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በማዘጋጀት በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ የሚወዳደሩበትን ዓይነት በፖስታው ላይ በመለየት በግዥና ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ 3:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 16ኛው ቀን በ3:30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 4:00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል::
- ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ያለተጨማሪ ወጪ እስከ ቢሮአችን በማምጣት የማስረከብ ኃላፊነት አለበት::
- የጨረታ መክፈቻ በበዓላት ወይም በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል::
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር- 046-881-3338 በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ::
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
አ/ምንጭ
✨ messages.ai_summary
Gamo Zone Finance and Plan Development Department seeks bidders to supply electric motorcycles, furniture, motorcycle tires, construction materials, printing, nitrogen jars, lime water with transport, veterinary drugs and medical supplies, and polyethylene tube/plastic bags. Bidders must have a valid business license, tax payment proof, TIN, supplier registration, and VAT proof.
