Tender Detail

Tender Details

  • Company SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 5 51 91 00
  • Websitehttps://www.filwuha.gov.et/
  • Deadline09 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Security25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ / CPO/ ብቻ
  • opening dateጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4:30 ይከፈታል::
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: በዚህ መሰረት:-

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ/የአገልግሎት ግዥ

  • ሎት 1 የባህላዊ ጠጅ አቅርቦት ግዥ
  • ሎት 2 ተቆልቶ የተፈጨ ቡና አቅርቦት ግዥ
  • ሎት 3 የተፈጨ ጤፍና ሩዝ አቅርቦት ግዥ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች በማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው::

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2018/2019 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ከሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
  3. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ / CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው::
  4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
  5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት:: ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሚልተው ማቅረብ አለባቸው::
  6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም:: ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት:: ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት::
  7. ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል::
  8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% ቀንሶ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል::
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4:30 ይከፈታል::
  10. ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሺያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ / Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል:: የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናንሺያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባ አለባቸው::
  11. የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካል ሠነድ ግምገማ ድርጅታዊ ብቃት እና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት 60% እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት 40% ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ:: ነገር ግን ቴክኒካል ናሙና ግምገማ ሠነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሻል ሠነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ:: የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል::

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ:- ስልክ ቁጥር 011 5 53 07 67/011 5 15 73 37

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
SPA Service Enterprise seeks bidders for supply of traditional beverages, roasted ground coffee, and ground teff and rice. Bidders must hold a valid trade license, TIN and VAT registration, tax clearance, and supplier registration with the Ministry of Finance and Economic Development.
Save Tender