በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ኮማ/ክ/ጦሮች 102ኛ፣ 103ኛ፣ 104ኛ እና105ኛ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የፅህፈት፣ የፅዳት፣ የህመማን ማገገሚያ እና የመኪና መለዋወጫ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ኮማ/ክ/ጦሮች
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ኮማ/ክፍለ ጦሮች ግ.ጨC001-2019
በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ኮማ/ክ/ጦሮች 102ኛ፣ 103ኛ፣ 104ኛ እና105ኛ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የፅህፈት፣ የፅዳት፣ የህመማን ማገገሚያ እና የመኪና መለዋወጫ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡-ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው ሊወዳደር ይችላል።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበቸው የጨረታ አይነቶች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /ከፋይነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማረጋገጫ ማቅረብየሚችል
- ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢፌዲሪ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
- አሸናፊ ድርጅቶች ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ያሸነፉትን ዋጋ ከጨረታው በኋላ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ እስከ 90 ቀናት ድረስ መቆየት ይኖርበታል፣
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲያቀርቡ የዕቃውን ሙሉ ስም፣ የተሰራበትን ሃገር እና የጥራት ደረጃውን (Specification)አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ስለሚጫረቱበቸው ለእያንዳንዱ ጨረታየጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው ብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ማቅረቢያ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የእቃውን አይነት ኢንቨሎፕ ላይ በግልፅ ማፃፍ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መምሪያ ጋር የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታውጆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አ/አ ኮየፈቼ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠ/መምሪያ ግቢ ውስጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነድ የሚገባው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ሲሆን በእለቱ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኮየ ፈቼ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠ/መምሪያ ግቢ ውስጥ 4:15 ይከፈታል 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- የመጫረቻ ሰነዱ የሚሸጥበት ቀን ከ 9/02/2019 እስከ 24/02/2019 ድረስ ነው።
- የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ኮማ/ክፍለ ጦሮች 102ኛ 103ኛ 104ኛ እና 105ኛ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር:- +251972665346 ወይም +251954318427 ይደውሉ።
በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ
ኮማ/ክ/ጦሮች
✨ messages.ai_summary
The Ministry of National Defense Special Operations Command (102nd–105th) seeks to procure stationery, cleaning supplies, medical recovery items, and vehicle spare parts via open tender. Eligible bidders must hold a valid business license, supplier registration certificate, tax payment proof, and VAT registration.
