የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በክፍት ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት
የክፍት ድርድር ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለወ/ሪት ጽዮን ጌታቸው የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛዋ በውሉ መሠረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በክፍት ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል::
| ተ.ቁ. | የንብረቱ ዝርዝር | ብዛት በቁጥር | የሐራጁ መነሻ ዋጋ | የንብረቱ ሁኔታ | ክፍት ድርድሩ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
| 1 | Baking Rotary Oven with Burner - Brand: PORLANMAZ, Model: PMDF200, Origin: Turkey | 1 | 10,370,520.53 | አዲስ | ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ጠዋት ከ4:00 እስከ 6:00 ሰዓት |
| 2 | Mixer - Brand: PORLANMAZ, Model: PMSP120, Origin: Turkey | 1 | |||
| 3 | Dough Divider - Brand: PORLANMAZ, Origin: Turkey | 1 | |||
| 4 | Dough Moulder Machine - Brand: PORLANMAZ, Model: PMD350፣Origin: Turkey | 1 | |||
| 5 | Proofer with Steam Generator - Brand: PORLANMAZ, Model: PMDF204, Origin: Turkey | 1 | |||
| Steamer - Model: PMCU10, Origin: Turkey | |||||
| 6 | Trolley with 14trays - Brand: PORLANMAZ - Number of pans per trolley – 16 - material – stainless steel | 4 | |||
| 7 | Bread Slicer - Brand: PORLANMAZ, Model: PMBS500, Origin: Turkey | 1 | |||
| 8 | Sound Proof Generator - Brand: AKSA, Model: AP33, Rated power: 33KVA | 1 |
የክፍት ድርድር ጨረታው መመሪያ
- በክፍት ድርድር ጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፣ የሚገዛበትን ዋጋ የሚገልጽ ማመልከቻ፣ የድርድር ጨረታውን መነሻ ዋጋ (20%) ብር 2,074,104.11 /ሁለት ሚሊዮን ሰባ አራት ሺ አንድ መቶ አራት ከአስራ አንድ ሳንቲም/ የያዘ በኢ/ት ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በመያዝ ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ጠዋት ከ4:00 ጀምሮ የኢ/ት ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ሎን ዎርክ አውት ዲቪዥን ቢሮ ማመልከቻውን በአካል ይዞ በመቅረብ ድርድር ማድረግ ይችላል::
- ንብረቱ የሚገኘው በሀዋሳ ከተማ፣መናኸሪያ ክ/ከተማ፣ጉዊ ቀበሌ ባንኩ ከሀዋሳ ጨርቃ ጨርቅ አ/ማ በተከራየው መጋዘን ውስጥ ነው::
- የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል::ፈቃዱን ካላገኘ ግን የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል::
- ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ/ በጥሬ ገንዘብ/ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች፣የንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ግብር እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ የታክስ ክፍያዎችን ጨምሮ ይከፍላል::
- የድርድር ጨረታው አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል::የድርድር ጨረታው አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው በድጋሚ ይካሄዳል::ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::
- ተጫራቹ በከፊል ዱቤ ለመከራየት አሸናፊ ከሆነ ባንኩ ማሸነፉን እንዲያውቅ ካደረገበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎችን መስማማት ይጠበቅበታል::
- የድርድር ጨረታው አሸናፊ አሸናፊ ሆኖ አስፈላጊውን ሂደት ካጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ወጪዎችን ማለትም የመጠለያ ኪራይ፣ የጥበቃ ክፍያ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ አለበት::
- የካፒታል ዕቃውን ካለበት መጋዘን ወደሚፈልግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ፣የጉዞ ኢንሹራንስ፣መትከያ፣ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው/ተከራይ ይሸፍናል::
- የድርድር ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር15 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቧቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት በኢ/ት ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ቢሮ ውስጥ ይደረጋል::
- ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ሎን ዎርክአውት ዲቪዥን በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 46 221 2789 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል::
- ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪክት ሎን ዎርክአውት ዲቪዥን ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በድርድሩ አይገደድም::
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት
✨ messages.ai_summary
Ethiopia Development Bank Hawassa District seeks to sell/lease by open bid various bakery machines and equipment (rotary oven, mixer, divider, moulder, proofer, steamer, trolleys, slicer, generator) on an as-is basis. Bidders must submit a renewed ID copy, price offer, and CPO; the asset is tax-exempt if the bank secures approval, otherwise the buyer pays tax.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
