Tender Detail

Tender Details

  • Company አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ
  • Address ከወንጂ ማዞሪያ ወደ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ 5 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ : አዳማ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-10-73-78-72
  • Website
  • Deadline02 Nov 2026, 1:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 2% (CPO)
  • opening dateበዚያው ቀን 8፡30
  • Categories Textile, Garment & Leather

በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ለጋርመንት ግብዓትነት የሚያውለውን 100% Cotton Canvas color olive በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ለጋርመንት ግብዓትነት የሚያውለውን 100% Cotton Canvas color olive በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት አለባቸው

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. በመንግስት የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው(የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት)
  3. የግብር ከፋይነት መለያ (Tin Card) ሰርተፍኬት ያላቸው
  4. ተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  5. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥ ብድን መሪ ዋና ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ )ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የአንዱን ዋጋ ከቫት በፊት ብቻ በመግለፅ ማስቀመጥ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፤
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 8፡30 በኢንዱስትሪያችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል ፤
  9. ጨረታው የሚከፈትበት በ15 ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ሰኞ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ኦርጅናል ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. ኢንዱስትሪው የተሻሉ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

አድራሻ፡- ከአዳማ ቆርቆሮ ነዳጅ ማደያ ወደ ወንጂ በሚወስደው መስመር 500 ሜትር ርቀት ላይ በስተግራ በኩል ፖ.ሣ.ቁ. 142
ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 25122 112 83 21 / 09 42 05 01 44

የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ

✨ messages.ai_summary
Adama Garment Industry seeks bidders for 100% cotton canvas in olive for garment input. Eligible bidders need a renewed trade license, government supplier certificate, TIN, and VAT registration. Financial and technical originals must be sealed in separate envelopes.
Save Tender