Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-558-2660
  • Website
  • Deadline18 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 25% (ብር 17,230,642.56) CPO
  • opening dateሕዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም 4:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)


የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር አማራ ባንክ/54/2019

አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም አበዳሪው ቅርንጫፍ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ የቦታው ስፋት የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር የንብረቱ ዓይነት/ የይዞታው አገልግሎት የጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ ቀን ሰዓት ቦታ
1 ብርፍሬ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ ማህበር ወ/ሮ አበባ ዩሃንስ እና አቶ ዩሃንስ ባዩ ፈለቀ አዲስ አበባ አዲስ አበባ ቦሌ 12 500M² ቦሌ12/53/10/108908/251466/02 ለመኖሪያ 68,922,570.25 ሕዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከ4:00 እስከ 5:00 ሰዓት አማራ ባንክ አ.ማ ዋናው መስሪያ ቤት

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት፣ በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
  3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡ ፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሃራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል፡፡
  4. የሐራጅ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፤ ግብር፤ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው/አሸናፊው/ ይከፍላል፡፡
  5. ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፤የመንጃ ፍቃድ፤ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል፡ ፡ ተጫራቾች የህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የሞና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሁፍ (የመተዳደሪያ ደንብ) ፤ ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
  7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካዉትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል፡፡
  8. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፤ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፤ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዥ ሰጪዉ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
  9. ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
  10. በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ፤ - እስከ 100% ብድር ሊያመቻች ይችላል ፡፡
    -በንብረቱ ላይ የምርት ተግባር ለሚያከናውኑ ገዥዎች ባንኩ ተጨማሪ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
    በተጨማሪም ለባንኩ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ባንኩ ለመደራደር ዝግጁ ነው፡፡
  11. የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጁ መዝጊያ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
  12. በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል፡፡
  13. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 0115 58 27 64 ወይም 011 5 58 41 89 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አማራ ባንክ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Amhara Bank is selling a 500m² residential property in Bole, Addis Ababa, via public auction. Bidders must submit a bank-certified C.P.O. for 25% of the starting price. The highest bidder wins upon written confirmation and must pay the balance within 15 days. Buyer pays all taxes, levies and transfer costs.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender