Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline20 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው ¼ (ብር 3,613,621.50) በንግድ ባንክ CPO
  • opening dateምዝገባ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 237 (414 ካ/ሜ ይዞታ) የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት አቶ ባወቀ እንዳለ እና በፍርድ ባለእዳ አቶ እንዳለ መላኩ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 25740 በቀን 10/10/2014ዓ.ም፣ በኮ/መ/ቁ.102636 በ26/08/2015ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.25740 በ15/09/2016ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.102636 በ11/3/2017ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በጉለሌ ክ/ከተ/ወረዳ 09 ውስጥ የሚገኘ የቤት ቁጥር 237 በይዞታ መለያ ቁጥር AA000100903846 የተመዘገበ ካርታ ያለው የይዞታ ስፋት 414ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 14,454,486 (አስራ አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሃምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ስድስት) ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ¼ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A 414 sq.m house (No. 237) in Gulele Sub-city, Woreda 09, is being sold at auction by the Federal Courts' Execution Office. Bidders must deposit 25% of the starting price via CPO from the Commercial Bank of Ethiopia; the winner must pay the full amount within 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender