Tender Detail

Tender Details

  • Company በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የ12ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline28 Oct 2026, 1:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየቀረበው ዋጋ 2% (CPO)
  • opening date18/2/2019 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Stationery Materials , Vehicle Spare Parts

የስራ ልብስና ጫማ፣ የጽህፈት፣ የትምህርት መርጃ፣ ቀለም፣ የፅዳት፣ የተሽከርካሪና የጄኔሬተር መለዋወጫ እና የግንባታ እቃዎች ግዥ (10 ሎቶች) - የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የ12ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የ12ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የ12ኛ ዕዝ ግዥ ክፍል በ2019 በጀት ዓመት በሎት 1 የተለያዩ የስራ ልብሶችና ጫማዎች፣ በሎት 2 የተለያዩ የጽህፈት እቃዎች፣ በሎት 3 የተለያዩ የትምህርት መርጃ እቃዎች፣ በሎት 4 የተለያዩ ቀለሞች፣ በሎት 5 የተለያዩ የፅዳት እቃዎች፣ በሎት 6 የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች፣ በሎት 7 የተለያዩ አላቂ የተሽከርካሪ እቃዎች፣ በሎት 8 የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መለዋወጫ እቃዎች፣ በሎት 9 የተለያዩ የጄኔሬተር መለዋወጫ እቃዎች፣ በሎት 10 የተለያዩ ለቤት ግንባታ የሚውሉ የግንባታ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፤
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤
  5. የዘመኑ ግብር የከፈሉ/ክሊራንስ/ ከጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣን/በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  6. ተወካይ ከሆነ /ከሆኑ/ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የእያንዳንዱን ዋጋ ቫት ሳይጨምር በመሙላት ደምሮ ከስር በኋላ የቫት ድምር ለብቻ መቀመጥ አለበት፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በአጠቃላይ የእቃ ዝርዝር በተናጠል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡
  10. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ፍሉይድ ከተጠቀመ ሰነዱ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ሰነዶችን መለየት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናሉን ፋይናንሻል ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታዎች፣ ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ የተወዳደሩበትን ዘርፍ በመፃፍ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. ለጨረታ ማስከበሪያ ከቀረበው ዋጋ ልክ 2% በባንክ ማዘዥ C.P.O ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  13. የጨረታ አሸናፊዎች ለውል ማስከበሪያ ካሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ ማዘዥ C.P.O ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  14. የጨረታ ሰነዱን ወልዲያ በሚገኘው የ12ኛ ዕዝ ፋይናንስ ቢሮ በስራ ቀንና ሰዓት ከ06/2/19 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 17/2/19 ዓ/ም ድረስ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  15. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በ18/2/19 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ ወልዲያ በሚገኘው የ12ኛ ዕዝ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ በቀን 18/2/2019 ዓ/ም ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት አዳራሽ ከቀኑ 7፡00 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  16. አሸናፊ የሆነው ተጫራች በሚሰጠው የዕቃ አቅርቦት ትዕዛዝ መሰረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን ማቅረብ የሚችል እና በዕዙ የጥራት ኮሚቴ ጥራቱ ከተረጋገጠ በኋላ ማስረከብ አለበት፡፡ የጥራት ኮሚቴው ካልተቀበለው ቀይሮ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  17. አሸናፊ የሆነው ነጋዴ ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ሪጅስተር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
  18. ዕዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. ግዥ ፈፃሚው በጀቱን በማረጋገጥ በዘርፉ 20% የመቀነስም ሆነ 20% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  20. በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለፁ ሌሎች ህጎች በግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የ12ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
The Ministry of National Defense's 12th Division General Directorate seeks to procure, via open tender across 10 lots: work clothing and footwear, stationery, educational materials, paints, cleaning supplies, vehicle spare parts and consumables, electronics and generator spares, and home construction materials. Bidders must hold a valid trade license, tax and VAT registration, and clearance certificates.
Save Tender