Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-558-2660
  • Website
  • Deadline29 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ ¼ (25%) CPO በአማራ ባንክ ስም
  • opening dateበየዕለቱ ከ4፡00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Disposal Sale

የመያዣ መኖሪያ ቤቶች (አዲስ አበባ የካ፣ ባህር ዳር) እና አይሱዙ NPR ተሽከርካሪ የሐራጅ ሽያጭ (አማራ ባንክ/53/2019) - አማራ ባንክ አ.ማ

Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)


የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር አማራ ባንክ/53/2019

አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ተ.ቁየተበዳሪው ስምየንብረት አስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍከተማክ/ከተማወረዳቀበሌየቦታው ስፋትየባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥርየንብረቱ ዓይነት/ የይዞታው አገልግሎትየጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ቀንሰዓት
1ኤ ቢ ኤስ ዜድ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበርአቶ ዘለቀ ማሞ ገብረማርያምደብረ ብርሀንአዲስ አበባየካ11-210 ካ.ሜAA000051101708መኖሪያ ቤት20,370,093.09ህዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ምከ 4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት
2ስንታየሁ፣እስብለው እና ጓደኞቻቸው ህብረት ሽርክና ማህበርአቶ ስንታየሁ ጥላዬ ፈረደግሽ አባይባህር ዳርአፄ/ቴ-11150 ካ.ሜአፄቴ/4676/2018መኖሪያ ቤት5,517,821.93ህዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ምከ 4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት
3ጥሩነህ ልጃለም አንዳርጌጥሩነህ ልጃለም አንዳርጌደጀንባህር ዳርአማራ ባንክ አ.ማ ባህር ዳር ዲስትሪክት-AA-02-C20537አይሱዙ (NPR)2,291,270.63ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ምከ 4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት፣ በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
  3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃልሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚገኘው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል፡፡
  4. የሐራጁ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፤ ግብር፣ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው /አሸናፊው/ ይከፍላል፡፡
  5. ተጫራቾች በሀራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፣የመንጃ ፍቃድ፣ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  6. ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
  7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርክፈሉትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል፡፡
  8. ጨረታው በሰንጠረዥ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪዉ ባይገኙ ጨረታው በዕለቱ ይካሄዳል፡፡
  9. ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚገኙ ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
  10. በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለጉትን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ፤
    • እስከ 100% ድረስ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
    • በንብረቱ ላይ የምርት ተግባር ለሚያከናውኑ ገዥዎች ባንኩ ተጨማሪ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡
    • በተጨማሪም ለባንኩ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ባንኩ ለመደራደር ዝግጁ ነው፡፡
  11. የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጁ መጀመሪያ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
  12. ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 0115 58 27 64 ወይም 0115-58 41 89 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ሴትና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅቶችም ያገለግላል፡፡

አማራ ባንክ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Amhara Bank is selling repossessed residential houses in Addis Ababa (Yeka) and Bahir Dar, plus an Isuzu NPR vehicle, via public auction. Bidders must register with a bank-certified payment document (CPO) covering 25% of the starting price, and present valid ID or legal entity documents.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender