ከዚህ በታች ስማቸው የተገለፁት ግለሰቦች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበደሩትን የብድር ገንዘብ በገቡት ውል መሠረት መክፈል ባለመቻላቸው ባንኩ ለብድሩ አመላለስ በዋስትና የያዛቸውን ተንቀሳቃሽ የመያዣ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የመያዣ ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ከዚህ በታች ስማቸው የተገለፁት ግለሰቦች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበደሩትን የብድር ገንዘብ በገቡት ውል መሠረት መክፈል ባለመቻላቸው ባንኩ ለብድሩ አመላለስ በዋስትና የያዛቸውን ተንቀሳቃሽ የመያዣ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የመያዣ ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪው /የመያዣ ሰጪው/ ስም | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የሚሸጠው ንብረት አይነት | የመያዣ ንብረት ዝርዝር መረጃ | የሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር) | የሐራጁ ደረጃ | ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት |
| 1 | ቴዎድሮስ አያና እርሻ ልማትድርጅት | በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግሥት ጋምቤላ ከተማ ባንኩ በተከራየው መጋዘን ቅጥር ግቢ | የእርሻ ትራክተር | ትራክተር ብራንዱ CASE ፤ሞዴል 110JX፤ የተመረተበት ዘመን 2015፤ ጉልበት 110HP | 506,490.95 | ሁለተኛ/2ኛ | ጋምቤላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ህዳር 4 ቀን 2019 ከረፋዱ 4፡00 እስከ 6፡00 |
| 2 | ኃይቶም ግደይ እርሻ ልማትድርጅት | በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግሥት ጋምቤላ ከተማ ባንኩ በተከራየው መጋዘን ቅጥር ግቢ | የእርሻ ትራክተር | ትራክተር ብራንዱ CLASS ፤ሞዴል 340C፤ የተመረተበት ዘመን 2015፤ ጉልበት 110HP | 416,406.25 | ሁለተኛ/2ኛ | ጋምቤላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ህዳር 4 ቀን 2019 ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡00 |
የሐራጅ መመሪያ
- የሐራጁ ተሳታፊዎች የሐራጅ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% /ሃያ አምስት በመቶ/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ( C.P.O) በማቅረብ በሐራጁ ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጫራቾች ከድርጅቱ የተሰጠውን ውክልና እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- በሐራጅ ሽያጭ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተበዳሪው እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡
- የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ሆኖም ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ተሰርዞ በድጋሚ የሐራጅ ሽያጩ እንዲወጣ ይደረጋል።
- በሐራጁ ለተሸናፊ ተሳታፊዎች ያስያዙት C.P.O ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ጨምሮ ሌሎች ገቢር እንዲከፍሉ በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያን ጨምሮ ይከፍላል፡፡
- ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ/በካሽ ብቻ ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚፈልግ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት፤ በስልክ ቁጥር፡ +251475512577፤ +251475512588፤ ወይም +251471518284 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም የሐራጁ ተሳታፊዎች ከጋምቤላ ዲስትሪክት ጋር በመነጋገር የጉብኝት ፕሮግራም ቀጠሮ በማስያዝ ፕሮጀክቱን መጎብኘት ይችላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት
✨ messages.ai_summary
Ethiopia Development Bank, Gambella District, invites bids for the auction sale of movable loan collateral: two agricultural tractors (CASE 110JX and CLASS 340C). Bidders must submit a bank-verified CPO for 25% of the starting price; company bidders need authorization and ID.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
