ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የወርክሾፕ ዕቃዎች እና የእጅ መሳሪያዎች ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር EC 001/2019
- ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የወርክሾፕ ዕቃዎች እና የእጅ መሳሪያዎች ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 - 6:30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7:30 -11:00 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴየሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200,00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት
- አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጎ
- አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጎ እንዲሁም፣
- ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከቶ የታሸገ መሆን አለበት፡፡
- በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የወርክሾፕ ዕቃዎች እና የእጅ መሳሪያዎች ግዥ የሚቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CP.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (Unconditional) ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተዘግቶ 4:45 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል፡፡
- ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-11-93-73-75 መጠቀም ይችላሉ፡፡
- ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኢትዮ አግሪ ሴፍት
ኃላ.የተ.የግ.ማህበር
✨ messages.ai_summary
Ethio Agri Safi is procuring workshop equipment and hand tools via open tender. Bidders must have a renewed business license, TIN, tax clearance certificate, supplier registration, and VAT registration certificate. Bids must include one original and one copy in separate sealed envelopes, both enclosed in one outer sealed envelope.
