የሸከላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት 3,003 ካ.ሜ የንግድና የመኖሪያ ልማት ቦታዎችን በሊዝ ለማስተላለፍ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት
የስድስተኛ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብከመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር የሸከላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሸከላ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ጠቅላላ ስፋቱ 3003(ሶስት ሺ. ሶስት) ካሬ ሜትር የሆነ ለንግድ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃድኛ የሆኑ ተጫራቶች :-
- የጨረታውን ሰነድ በሸከላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማትና ባንክ ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ቦታወቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታውን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን / Specifection/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 50 በመቶ ያላነስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ከፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 50 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።
- ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብከመ በኦ/ብ/ ዞን በሸከላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማትና ባንክ ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን 04/02/2019 ዓ.ም እስከ 17/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ17/02/2019 ዓ.ም 11:00 ሰዓትይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ 18/02/2019 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት በሸከላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት የሸከላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከትይችላሉ፡፡
- የአካበቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ የሸከላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከትይችላሉ፡፡
- የሸከላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨረማሪ መረጃ :-በስልክ ቁጥሮች
0920960730/0923661118 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት
✨ messages.ai_summary
Shekla Town Sub-Municipality invites eligible bidders to a lease auction of 3,003 sq.m of land in Shekla Town for commercial and residential development. Bidders must submit documents per specifications, pay a non-refundable fee, and provide a CPO bid security of at least 50% of the lease base price.
