Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ የግዳን ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline23 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityሎት 1,3,4,5,6,8,9: ብር 40,000 ፤ ሎት 2,7: ብር 10,000 (CPO/ጥሬ ገንዘብ/ባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateበዚሁ ቀን 4፡30 ሰአት ይከፈታል
  • Categories Furniture , Stationery Materials , Construction Materials And Raw Materials

የግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችና የግንባታ ማቴሪያሎች ግዥ ጨረታ

በአብክመ የግዳን ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019

በአብክመ በሰ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት ለግ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በመደበኛ በጀት ፡- ሎት1፡- የጽህፈት መሳሪያ ፤ ሎት፡-2 ቋሚ አላቂ የቢሮ መገልገያ ሎት፡-3 የሚገጣጠም ፈርኒቸር ሎት፡-4 ኤሌክትሮኒክስ እቃ ሎት፡-5 የመኪና ጎማ ሎት፡-6 የመኪና መለዋወጫ እቃወች ሎት፡-7 የጽዳት እቃዎች ሎት 8፡- የግንባታ እና የውሃ እቃዎች ማቴሪያል ሎት 9፡- ስሚንቶ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድና ምዝገባ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ተወዳዳሪዉ በግብር አመቱ ተገቢዉን የታክስ እና ግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል እና ላለማጭበርበር እና ላለመመሳጠር የሚሰጠውን ፎርም ሞልቶ ማቅረብ አለበት፤፤
  3. የግዥ መጠኑ ከ500000 ( አምስት መቶ ሺህ ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆነና መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ላይ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ(ማስገባት) አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የተሰጣቸዉን የጨረታ ቅፅ በአግባቡ መሙላት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር /በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዚህ በታች በዝርዝር በተገለጸው መሰረት ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ድረስ ያሉት ሁሉም ሎቶች 10 ኛዉ ቀን 11፡30 ድረስ ግ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 001 ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት በመምጣት መግዛት ይችላሉ ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ የሚወዳደሩበት እቃ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሎት1- የጽህፈት መሳሪያ ሎት፡-3 የሚገጣጠም ፈርኒቸር ሎት፡-4 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 5 የመኪና ጎማ ሎት፡-6 የመኪና መለዋወጫ እቃወች ሎት 8፡- የግንባታ እና የውሃ እቃዎች ማቴሪያል ሎት 9፡- ስሚንቶ ጨረታ ብር 40000 / አርባ ሺህ ብር/ እና ፤ሎት፡-2 ቋሚ አላቂ የቢሮ መገልገያ ሎት፡-7 የጽዳት እቃዎች ብር 10000 / አስር ሺህ/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ ሲ.ፒ.ኦ፤ ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ጋራንት በማስያዝ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ አሽጎ (አያይዞ) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  8. ጨረታዉ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 40 አርባ ቀን የሚቆይ ይሆናል ፡፡
  9. ጨረታዉ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታዎች ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ድረስ ያሉት በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰአት ይከፈታል ፡ ፡ የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ውጤቱ በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 10% በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ ሲ.ፒ.ኦ፤ ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ጋራንት በማስያዝ በፍትህ ዉለታ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
  11. የሚገዙት እቃዎች የማስረከቢያ ቦታ ግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ባሉ ሁሉም ንብረት ክፍሎች ዉስጥ ይሆናል፡፡ ለዚህ ም የሚወጡ ወጭዎች በሙሉ በአሸናፊዉ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፤፤
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ መረጃ ካስፈለገ በግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0332120008 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአብክመ የግዳን ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Gedan Woreda Finance Office invites bids for office supplies, furniture, electronics, vehicle tires and spare parts, cleaning materials, construction and water materials, and cement, under Lots 1–9. Bidders need a valid trade license, tax clearance, and anti-fraud form; VAT registration is required for purchases above 500,000 birr.
Save Tender