Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline23 Oct 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሦስት መቶ ብር)
  • Bid Securityከጠቅላላ ዋጋ 0.5%
  • opening dateበተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል
  • Categories Construction Equipment And Machinery , Construction Materials And Raw Materials

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ለቱቦ ሥራ የሚሆን ሞልድ ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር፡- ሲ/መ/ባ/003/2019

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ለቱቦ ሥራ የሚሆን ሞልድ ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁየዕቃው አይነትብዛት
1ሞልድ Ø80 ሴ.ሜትር8
2ሞልድ Ø90CM ሴ.ሜትር8
3ሞልድ Ø1 ሜትር8
4ሞልድ Ø1.2M ሜትር8

በዚሁ መሠረት፡-

  1. የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አቅራቢነት ፍቃድ ያላቸው
  2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ከሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10(አስር) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ(CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Unconditional Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 0.5% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሠረት ይሆናል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበርያ /Bid Security/፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸዉ ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካትተው በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማሕተም በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446

ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
ሀዋሳ

✨ messages.ai_summary
Sidama Roads Authority seeks to buy pipe molds for road construction projects: Ø80cm, Ø90cm, Ø1m, and Ø1.2m, 8 each. Eligible suppliers must hold a valid construction equipment supply license, business license, VAT and tax registration, tax clearance, and government supplier registration.
Save Tender