Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline12 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ግምቱ 1/4 (ብር 357,153.50) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ CPO
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Disposal Sale

በየካ ክ/ከተማ (ለሚ ኩራ) G+10 አፓርትመንት የምድር ወለል 49.1 ካ/ሜ የንግድ ሱቅ የሐራጅ ሽያጭ (መነሻ ብር 1,428,614) - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፀፀም ጽ/ቤት

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አቶ ናትናኤል አብርሃም እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ሃና ሩሶም መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.299412 በቀን 26/6/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ እና በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.321201 በቀን 5/3/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጊፍት ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ ላይ በየካ ክ/ከተማ ቀበሌ 03 በአዲሱ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሚገኝ ባለ 45 አባወራ G+10 አፓርትመንት በሳይት ቁጥር 3 የምድር ወለል ላይ የሚገኝ ሱቅ ስፋቱ 49.1 ካ/ሜ የንግድ ሱቅ ስፋቱ 49.1 ካ/ሜ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,428,614 ( አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ አስራ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፀፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Sale by auction of a 49.1 sq.m ground-floor commercial shop in a G+10 apartment (Lemi Kura, Yeka) by the Federal Courts Execution Office. Bidders must deposit 1/4 of the starting estimate via CPO; the buyer pays transaction tax.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender