Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Orthodox Tewahido Church-Child and Family Affairs Organization Genete Eyesus Child and Family Development Program Coordination Office
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 0111142948
  • Website
  • Deadline19 Oct 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 400.00 (የማይመለስ)
  • Bid Security2% (CPO)
  • opening dateበእለቱ ከሰዓት በኋላ 8፡00
  • Categories Printing And Publishing , Stationery Materials

ለአንደኛ ደረጃ ት/ቤት 1,450 የማጣቀሻ መፅሐፍት ግዥ - የገነተ ኢየሱስ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኢኦተቤ ሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት)

Ethiopian Orthodox Tewahido Church-Child and Family Affairs Organization Genete Eyesus Child and Family Development Program Coordination Office


የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የገነተ ኢየሱስ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚሆኑ የማጣቀሻ መፅሐፍትን 1,450/አንድ ሺ አራት መቶ ሃምሳ/ አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ የዘመኑ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው
  2. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት መኖር አለበት
  4. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአምስት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በሚያስገቡበት ጊዜ በጨረታ ሰነዱ ላይ ባቀረበው የመፅሐፍ አይነትና ዋጋ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ጨረታውን አሸናፊ ድርጅት ለአንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሚሰጥ የማጣቀሻ መፅሐፍትን በአዲስ አበባ ከተማ ውል ከተፈራረመበት ዕለት ጀምሮ በ2 /ሁለት/ ቀናት ውስጥ በራሱ ትራንስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  9. የመፅሐፎቹ ብዛት በሚሰጠው ዋጋ መሰረት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፡፡
  10. ጨረታው ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም. 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከሰዓት በኋላ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-14-29-48 መጠየቅ ይቻላል፡፡
  13. CPO የሚሰራበት ስም EOC – CFAO Genete Eyesus Child and Family Development Program Coordination Office በሚል ይሆናል፡፡

አድራሻ
በየካ ክ/ከ ወረዳ 1 ከገነተ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ዝቅ ብሎ ወደ ፈረንሳይ አምባሲ በሚወስደው መንገድ ሚያዚያ 23 ት/ቤት ጎንደርስ ከሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የገነተ ኢየሱስ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Procurement of 1,450 reference books for a primary school by the Ethiopian Orthodox Tewahido Church Child and Family Affairs Organization, Genete Eyesus Program Office. Bidders need a valid business license, supplier registration certificate, TIN, and VAT registration. Books must be delivered in Addis Ababa within 2 days of contract signing.
Save Tender