Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline22 Oct 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityከጠቅላላ ዋጋ 0.5% (ከብር 500,000 አይበልጥም) (CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Categories Vehicles Rent

የሰርቪስ መኪና ኪራይ አገልግሎት (ደብል ጋቢና፣ ሚኒ ጋቢና እና ሚኒባስ) ግዥ (ሲ/መ/ባ/001/2019) - የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


የመጀመሪያ ዙር የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡-ሲ/መ/ባ/001/2019
የሰርቪስ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

መ/ቤታችን የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታና ጥገና ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ደብል ጋቢና ሚኒ ጋቢና እና ሚኒ ባስ መኪናዎችን ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

ሎትየመኪናዉ አይነትብዛትጠቅላላ ተሽከርካሪ የሥራ ቀንየሥራ ቦታ
1ደብል ጋቢና41080በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ዞን
ሚኒ ጋቢና41080
2ሚኒባስ1270በዳዬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት የሥራ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00(ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር)ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር -5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Unconditional Bid) ከጠቅላላው ዋጋ 0.5% ሆኖ ከ500,000 ብር በላይ የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000 ብቻ CPO ወይም ባንክ ጋራንት በማሰራት ለብቻዉ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. የሰሪት ዘመናቸው ለሚኒ እና ደብል ጋቢና እ.አ.አ 2008 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ሚኒባስ እ.አ.አ 2010 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው ፡፡
  5. ከዚህ በፊት ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ማሽነሮችን ወደ ስራ ያላስገባና ውላቸው የተቋረጠ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ /Bid Security/፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ዉስጥ ተካተዉና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማክበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ያለበት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፣ 0462-128-446

ሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን
ሀዋሳ

✨ messages.ai_summary
Sidama Roads Authority seeks eligible bidders to rent double cabin, minicabin, and minibus vehicles for road construction and maintenance projects in Sidama region. Bidders must provide valid business license, VAT and TIN certificates, tax clearance, and supplier registration. Vehicles must meet minimum age requirements.
Save Tender