Tender Detail

Tender Details

  • Company Berhan Bank S.C (ብርሃን ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116185683
  • Websitehttps://berhanbanksc.com/
  • Deadline09 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (ሲፒኦ)
  • opening dateጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

በዳምቦያ ከተማ የሚገኝ 204 ካ.ሜ የንግድ ቤት የሐራጅ ሽያጭ - ብርሃን ባንክ አ.ማ

Berhan Bank S.C (ብርሃን ባንክ አ.ማ)


ብርሃን ባንክ አ.ማ
BERHAN BANK S.C
የሐራጅ ማስታወቂያ

ብርሃን ባንክ አ.ማ ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን የ1/4 (አንድ አራተኛ) (ሲፒኦ) በብርሃን ባንክ አ.ማ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን እንዳሸነፈ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ አለበት፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
  3. የንግድ ቤቱ ጨረታ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይከናወናል፡፡
  4. የጨረታ አሸናፊው በሚገዛው ንብረት ላይ የሚፈለግ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያዎች እና የሊዝ ክፍያዎች ይመለከተዋል፡፡
  5. መያዣ ሰጪዎች ሐራጁ በሚከናወንበት ቦታ ቀንና ሰዓት መገኘት ይችላሉ፡፡ ባይገኙ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
  6. በባንኩ ብድር መምሪያ መስፈርት መሰረት እና በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የሚፈለጉበትን ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  7. ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይቻላል፡፡
  8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

የንግድ ቤት

ተ.ቁየተበዳሪዉ ስምየመያዣ ሰጭዉ ስምመኖሪያ/ የንግድ ቤት የሚገኝበት አድራሻየቦታው ስፋት በካሬ ሜትርየንብረቱ አገልግሎትየባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥርየጨረታ መነሻ ዋጋጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት፤
1አቶ ቢኒያም ተሰማ ኤርጊቾአቶ ቢኒያም ተሰማ ኤርጊቾዳምቦያ ከተማ 01 ቀበሌ204 ካ.ሜየንግድ ቤትዳ/ከ/ማ/00/761,000,000.00ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30

በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሰረት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ፤

  1. ለ፤ አቶ ዘላለም ኃ/ማሪያም ሰንበቱ እና ወ/ሮ ፍሬህይወት ከበደ

    ስማችሁ ከላይ የተጠቀሰው የብርሃን ባንክ አ.ማ ተበዳሪ በገባችሁት የብድር እና/ወይም መያዣ ውል መሠረት መክፈል የሚጠበቅባችሁን ክፍያ ባለመክፈላችሁ ምክንያት ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ባስመዘገባችሁት አድራሻ ልትገኙ ያልቻሉ እና ማስጠንቀቂያውን ለመውሰድ ፍቃደኛ ባለመሆናችሁ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት አልተቻለም፡፡

    ስለሆነም ይህ ማስጠንቀቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ ያለባችሁን ቀሪ ዕዳ አጠናቃችሁ እንድትከፍሉ እየጠየቅን፤ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ መክፈል ካልቻላችሁ ባንኩ በአዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት እርምጃ የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011-6506900 እና 011-6506276 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

ብርሃን ባንክ አ.ማ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!

✨ messages.ai_summary
Berhan Bank is selling a commercial shop in Damboya town, 204 sq.m, by public auction. Bidders must deposit 1/4 of the starting price as CPO. The winner must pay the full price within 15 days. Government taxes, VAT, transfer and lease fees apply.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender