ፍርድ ያረፈበት ቤት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤ/ቁ/MH14 በሐራጅ ይሸጣል - በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ እመቤት ገዛሐኝ እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ምናሴ ለማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/73388 በ7/2/2012 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/91208 በ19/06/2012 ዓ/ም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.91208 በቀን 27/09/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት ቤት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤ/ቁ/MH14 ተጠሪ ስም ተመዝግቦ ያለ ቤት በወ/ሮ አጸገነት አባተ ስም የተዘጋጀ የካርታ ቁጥር 39963/A/112 በሰሪያል ቁጥር 193548 የሚታወቅ የቦታ ስፋት በካርታ መሰረት 834 ካ/ሜ በአካል 828 ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 26,684,596 ( ሃያ ስድስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ስድስት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጣቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመሰወድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን ፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጥ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
