Tender Detail

Tender Details

  • Company ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address 22 ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251118212214
  • Website
  • Deadline29 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceየማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 1,500,000.00 (CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 7-02
  • Categories Vehicle

Middle Floor Manual Transmission Bus (የማስልመኛ አውቶብስ) ግዥ - አአከአአድ/ብግጨቁ/016/2019 - አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

አአከአአድ/ብግጨቁ/016/2019

አዲስ አበባ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/016/2019 Middle Floor Manual Transmission Bus (የማስልመኛ አውቶብስ) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፦

  1. በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)፤
  2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፤
  3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፤
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ኮፒ (VAT Certificate)፤
  5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፤
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 1,500,000.00 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) በማቅረብ በግልጽ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአምስተኛ ቀንጃ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 አያት ሀንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (መስከል) የግዥ ዲይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ይዘውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዲይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፤

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡ 0116663206

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Bus Service Enterprise seeks to buy Middle Floor Manual Transmission Buses via national open tender. Eligible suppliers must be licensed in the field and submit a valid trade license, supplier registration, tax registration, VAT certificate, tax clearance, and a bank-guaranteed CPO or bank guarantee.
Save Tender