Tender Detail

Tender Details

  • Company ZEMEN CONSTRUCTION CORPORATION (ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
  • Address ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 (ባህር ዳርዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንጻ አካባቢ የቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት አ.ማ ግቢ ውስጥ) እና አዲስ አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-218-0538
  • Websitehttps:// zcc.org.et
  • Deadline23 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityቫትን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም / unconditional bank guarantee/
  • opening dateበእለቱ 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል
  • Categories Finishing Work , Metals And Metal Working , Finishing Materials

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን – ለፌዴራል ገቢዎች ባህር ዳር ቅርንጫፍ ግንባታ ፕሮጀክት የአልሙኒየም ፓነል፣ የደረጃ የእጅ መደገፊያ፣ የተለያዩ ሲሊንግና ክላዲንግ እቃዎች አቅርቦትና ገጠማ ጨረታ (ቁጥር 13/2019 እና 14/2019)

ZEMEN CONSTRUCTION CORPORATION (ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 13/2019 እና 14/2019

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ውል ይዞ ለሚገነባው ሰፌደራል ገቢዎች ባ/ዳር ቅርንጫፍ ግንባታ ፕሮጀክት፡-

1, Supply and Fix Aluminum Panel, Stair case hand rail & baluster Aluminum አቅርቦትና ገጠማ ስራ በጨረታ ቁጥር 13/2019፣

2. Supply and Fix SUSPENDED METAL CEILING PANEL, GYPSUM BOARD CEILING, WOODEN GEILING UV BOARD CLADDING and WPC Clading አቅርቦትና ገጠማ ስራ በጨረታ ቁጥር 14 /2019 ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት እና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣

በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ ፈቃድ ለማደስ ግብር ስለመከፈላቸው የሚስተ ማስረጃ ያለው/ያላት፣ አቅርቦት እና ገጠማ ሥራ ከዚህ በፊት ለመስራታቸው ህጋዊ ከሆነ ተቋም የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣

ጨረታ ማስከበሪያ ቫትን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም / unconditional bank guarantee/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣

ጨረታ ሰነዱ ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፣

የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ባ/ዳር ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእለቱ 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ባህር ዳር ዋናው ቢሮ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 የግን ብግቨርና አቅርቦት ቡድን አስተባባሪ ቢሮ ክፍል ነው፡፡

ውድድሩ በሎት/በጥቅል ዋጋ የሚታይ ይሆናል፣ ዝርዝር የጨረታ መመሪያው እና የውል ይዘቱ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው

ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ባ/ዳር 0582180538 /09-18-01-06-17/ 09-13-27-60-57
አዲስ አበባ -- 011-126-5652/ 5145 /0918800364

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን

✨ messages.ai_summary
Zemen Construction Corporation seeks suppliers/contractors to supply and install aluminum panels, staircase handrails and balusters, suspended metal ceiling panels, gypsum board ceilings, wooden ceilings, UV board cladding and WPC cladding for a Federal Revenues Bahir Dar branch building project. Bidders need a valid trade license, TIN, VAT registration, and prior supply-and-installation experience.
Save Tender